አልወድህም ውሸቴን ነው አልወድህም ምርጡን ጊዜ አልሰጥህም ብሰጥህም................. የድካሜን… — #KALTUBE — TG.ME

አልወድህም

ውሸቴን ነው አልወድህም
ምርጡን ጊዜ አልሰጥህም
ብሰጥህም.................
የድካሜን ጥፍጣፊ
የሃሳቤን ትርፍራፊ

ውሸቴን ነው አልወድህም
ሙሉ ልቤን አልሰጥህም
ብሰጥህም................
የሰው ምርኩዜን ስቀማ
ባመንኩትኝ ሰው ስደማ

ምጠይቅህ ያ ጩኸቴ የማልዋሽህ አንድ እውነቴ
የእውነት መኖር ስለማልችል ይሙትልኝ እኔነቴ
ትግሌን ልስቀል ....ብቻህን ኑር በህይወቴ!

https://t.me/Tzamamovment
❤22👏3🙏1
June 3, 2026 2.8K 10