ሀቢቢ ግማሹ ኩራተኛ ነው ይልሃል፡፡
ሌላው እንደርሱ ያለ ትሁት ሰው ገጥሞኝ አያውቅም ይላል፡፡
አንዳንዱ ገና ስምህ ሲነሳ በርግጎ ይጠፋል፤ ሌላው ስላንተ አውርቶ አይጠግብም፡፡
ከፊሉ ያንተን መገኛ ሲያስስ ይውላል፤ ሌላው አንተ ያለህበት ምቾት አይሠጠዉም ይሸሻል፡፡
በአንድ አቋምህ ብቻ አንቅረው የተፉህ እንዳሉ ሁሉ፤
በአንድ አቋምህ የተነሳ ከልባቸው ሊያወጡህ የተቸገሩ አሉ፡፡
አንዳንዱ ለትችትህ ሲሽቀዳደም ሌላው ሲያድንቅህ ዉሎ ቢያድር አይደክመዉም፡፡
አንዱ እሱ ጥሩ ሰው ነው ሲልህ፤ ሌላው በጣም መጥፎ ነው ብሎ ይሞግታል፡፡
አውቀዋለሁ መልካም ሰው ነው የሚል እንዳለ ሁሉ አታውቁትም መሰሪ ሰው ነው ብሎ የሚከራከርም አለ፡፡
ያለምክንያት እንደሚጠሉህ ያሉትን ያህል ያለምክንያት የሚወዱህም ብዙ ናቸው፡፡
ይህ ሁሉ ታድያ አንድ አንተው ብቻ መሆንህን ልብ በል።
አንተ አንድ ነህ፤
ሰዎች ላንተ ያላቸው እይታ ግን ብዙ ነው።
የተለያየ መልክን ስብእና ይዘህ በሰዎች ልብ ዉስጥ ትኖራለህ፡፡
ሁላችንም እንደዚያው ነን፡፡
አይግረመን ወዳጆቼ ፡፡
ብቻ ትክክል ለመሆን እንጣር፣
እውነትን ይዘን እንኑር፣
አላህን አስበን እንሥራ፡፡
ለአላህ ስንሠራ የሰዎችን ጉዳይ የሚያስተካክልልን እሱ ነው፡፡
ቢሆንም ቢሆንም ብቻ ይገርማል የአላህ ሥራ፡፡
t.me/muselimnegn














