16 ምርጥ የAI መተግበሪያዎች ፦ ** 1. Elicit.com — ለምርምር ሥራዎች የሚያገለግል የኤአይ… — Info Tech — TG.ME

16 ምርጥ የAI መተግበሪያዎች  ፦
**
1. Elicit.com — ለምርምር ሥራዎች የሚያገለግል የኤአይ መተግበሪያ ሲሆን የምርምር ጽሑፎችን በፍጥነት ይፈልጋል። የሚፈለጉ መረጃዎችን ለይቶ ያወጣል፤ ማጠቃለያዎችን ለመሥራት ያስችላል፡፡

2. Otter.ai — በድምፅ የተቀረጹ መረጃዎችን፣ ንግግሮችን በቀጥታ ወደ ጽሑፍ የሚቀይር የድምፅ-ወደ-ጽሑፍ ሶፍትዌር ነው፡፡

3. Decktopus.com — አርዕስት እና መረጃ ብቻ በመስጠት በአጭር ጊዜ ውስጥ ውብ እና ሙያዊ የሆኑ የፓወር ፖይንት ማቅረቢያዎችን (Slides) በኤአይ የሚሰራ መተግበሪያ ነው፡፡

4. Gitmind.com — ሀሳቦችን፣ ዕቅዶችን እና ፕሮጀክቶችን በምስላዊ የሀሳብ ካርታ (Mind Map) እና በሥራ ፍሰት ንድፎች መልክ ለማደራጀት ያገለግላል፡፡

5. Lightpdf.com — የፒዲኤፍ (PDF) ፋይሎችን አርትኦት ለመስራት፣ ለመለወጥ፣ ለማዋሃድ እና በፋይሎቹ ላይ ፊርማ ለማስቀመጥ የሚያስችል የኤአአይ መተግበሪያ ነው፡፡

6. Picwish.com — የፎቶዎችን ጀርባ (Background) ለማስወገድ፣ የምስል ጥራትን ለማሻሻል እና አላስፈላጊ ነገሮችን ከምስል ላይ ለማንሳት የሚያስችል የፎቶ ማስተካከያ ኤአይ ነው፡፡

7. Reccloud.com — ስክሪን ለመቅረፅ፣ ቪዲዮዎችን ለማጫወት እና በኤአይ ታግዞ አጫጭር የቪዲዮ ይዘቶችን ለመፍጠር የሚያገለግል ፕላትፎርም ነው፡፡

8. Kapwing.com — ቪዲዮዎችን ለመቁረጥ፣ የግርጌ ጽሑፍ (Subtitle) ለመጨመር እና ይዘቶችን በማህበራዊ ሚዲያ መልክ ለማዘጋጀት የሚያስችል የኦንላየን ቪዲዮ ማስተካከያ ነው፡፡

9. Podcastle.ai — የፖድካስት ድምፆችን ለመቅረፅ፣ የጀርባ ጫጫታዎችን ለማስወገድ እና ጥራታቸውን ጠብቆ ለማዘጋጀት የሚረዳ የድምፅ ማስተካከያ ኤአይ ነው፡፡

10. Consensus.app — ሳይንሳዊ ጥያቄዎችን ሲጠይቁ ከታመኑ የምርምር ጽሁፎች በማስረጃዎች የተደገፉ መልሶችን ፈልጎ የሚያቀርብ የኤአይ መተግበሪያ ነው፡፡

11. Researchrabbit.ai — በተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ተመሳሳይ የምርምር ጽሁፎችን ለመፈለግ እና ጽሁፍን በግራፍ መልክ ለማሳየት የሚያገለግል ነው፡፡

12. Zotero.org — ለምርምር ሥራዎች የሚያስፈልጉ መጻሕፍት እና የጽሑፍ ምንጮችን (References) ለማደራጀት፣ ለማስቀመጥ እና ለመጥቀስ የሚያገለግል ነፃ የኤአይ መተግበሪያ ነው፡፡

13. Scite.ai — የምርምር ጽሁፎች በሌሎች ተመራማሪዎች እንዴት እንደተጠቀሱ (በድጋፍ፣ በተቃውሞ ወይም በጥቀስ መልክ) ለመተንተን የሚያስችል መተግበሪያ ነው፡፡

14. Scholarcy.com — ረጅም የምርምር ጽሁፎችን፣ መጻሕፍት እና ሪፖርቶችን በማንበብ ዋና ዋና ነጥቦቻቸውን በአጭሩ አጠቃልሎ የሚያቀርብ መተግበሪያ ነው፡፡

15. Connectedpapers.com — የአንድን የምርምር ርዕስ መነሻ በማድረግ ተዛማጅነት ያላቸውን ሌሎች ጥናቶች በምስላዊ ካርታ መልክ የሚያሳይ መተግበሪያ ነው፡፡

16. Writefull.com — ለአካዳሚክ እና ለሳይንሳዊ ጽሑፎች የተዘጋጀ የሰዋስው፣ የስፔሊንግ እና የቃላት አጠቃቀም ማስተካከያ የኤአይ መተግበሪያ ነው፡፡

Ayu ዘhabesha
August 30, 2026 94 1