በቅርቡ ይፋ የሆነውን የሳምሰንግ አዲስ ታጣፊ ስልክ Galaxy Z Fold 8 Review
ስልኩ አጠቃላይ rating 8.9 / 10 ከፍተኛ ነጥብ ያገኘ ሲሆን ዘንድሮ ሳምሰንግ የDesign ለውጥ ካደረገባቸው ስልኮች ቀዳሚው ነው።
ስልኩን ከቀደሙት የFold ስልኮችና ከUltra series የበለጠ ተመራጭ አድርጎታል ብሏል።
⚫️አዲስ Aspect Ratio (Passport Shape): የቀደሙት የFold ስልኮች ረዥምና ጠባብ ነበሩ። Z Fold 8 ግን አጭርና ሰፊ (Wider) ሆኖ ተሰርቷል።
⚫️የውጪ ስክሪን (Cover Screen): 5.5-inch AMOLED (10:16 aspect ratio) ሲሆን እንደ ፓስፖርት ሰፋ ያለ በመሆኑ ስልኩን ሳትከፍቱት መልእክት ለመጻፍ እና ካርታ ለማየት በጣም ይመቻል።
⚫️የውስጥ ስክሪን (Main Display): 7.6-inch AMOLED (4:3 aspect ratio) አለው። ይህም ቪዲዮዎችን ሲያዩ የሚፈጠረውን ጥቁር ፍሬም (Letterboxing) ይቀርፋል።
ለGamingና ለMultitasking በጣም ምቹ ነው።
⚫️Flex Titanium & Anti-Glare Coating: በስክሪኑ ስር Titanium alloy የተጨመረበት ሲሆን የስክሪኑ መታጠፊያ መስመር ከበፊቱ በበለጠ እንዳይታይ አድርጎታል። አዲሱ Anti-glare coating ደግሞ የፀሐይ ብርሃን ነጸብራቅን ይከላከላል ተብሏል።
⚫️ቀላልና ቀጭን፦ ስልኩ በታሪክ ቀላል የተባለው የFold ስልክ ሲሆን ክብደቱ 201 ግራም ብቻ ነው። ሲታጠፍ 9.7mm ውፍረት አለው።
🚀 ዋና ዋና specificationና Performance
⚫️Processor: በቅርቡ የወጣው Snapdragon 8 Elite Gen 5 ቺፕሴት ተገጥሞለታል።
⚫️RAM & Storage: እስከ 16GB RAM እና 1TB Storage
⚫️Battery: 4,800mAh
⚫️Brightness: የሁለቱም ስክሪኖች Peak Brightness እስከ 3,000 nits ይደርሳል።
⚫️Durability: IP48 Dust & Water resistance Gorilla Glass Victus 2 እና 3 ተጠቅሟል።
ደካማ ጎኖች (Cons):
ስልኩ በጣም ውድ የሚባል ሲሆን ዋጋውም ከ1,900 ዶላር ጀምሮ ይሸጣል ተብሏል።
ሌላው Dedicated Zoomና Telephoto Camera የለውም። 50MP Main + 50MP Ultra-wide ብቻ ነው ያለው።
እንደ MagSafe ያሉ Magnetic accessories ለመጠቀም ተጨማሪ Case ያስፈልገዋል።
✍sucesstube
2August 13, 2026 193