ማንኛውንም አፕሊኬሽን ወይም ሶፍትዌር (ለምሳሌ፦ Telegram for Desktop, CapCut, VLC… — Info Tech — TG.ME

ማንኛውንም አፕሊኬሽን ወይም ሶፍትዌር (ለምሳሌ፦ Telegram for Desktop, CapCut, VLC Media Player ወይም WinRAR) ለማውረድ ጎግል (Google) ላይ ፈልገው ያውቃሉ? ሰርች ሲያደርጉ መጀመሪያ የመጣውን ሊንክ ተጭነው ካወረዱ፣ ትልቅ ወጥመድ ውስጥ ወድቀው ሊሆን ይችላል!
በአሁኑ ሰዓት የሳይበር ሌቦች እኛን ለማጥመድ ጎግልን ራሱን በገንዘብ እየገዙት ይገኛሉ። ይህ አደገኛ ስልት በሳይበር ደህንነት "Malvertising" (Malicious Advertising) ይባላል።

🚨 ጥቃቱ እንዴት ነው የሚሰራው?
እኛ ጎግል ላይ የአንድ ሶፍትዌር ስም ጽፈን ስንፈልግ፣ ጎግል መጀመሪያ ላይ "Sponsored" ወይም "Ad" (ማስታወቂያ) የሚል ምልክት ያላቸውን ሊንኮች ያመጣልናል።

ሌቦቹ የራሳቸውን ቫይረስ ያለበትን ድረ-ገጽ ይፈጥሩና ልክ የእውነተኛው ሶፍትዌር ድረ-ገጽ እንዲመስል ያደርጉታል። ከዚያም ለጎግል ገንዘብ በመክፈል የእነሱ የውሸት ድረ-ገጽ ከእውነተኛው ድረ-ገጽ በላይ መጀመሪያ መስመር ላይ እንዲቀመጥ ያደርጋሉ።

💡 አደገኛው ነገር፦ ሰዎች ጎግል መጀመሪያ ያመጣውን ሊንክ ሁልጊዜ እውነተኛ ስለሚመስላቸው ሳያስተውሉ ይጫኑታል። የሚወርደው ሶፍትዌር በትክክል ስራውን ቢሰራም፣ በጀርባ ግን የስልካችንን እና የኮምፒውተራችንን የባንክ ፓስወርዶች፣ ክሪፕቶ ቫሌቶችን እና የሶሻል ሚዲያ አካውንቶችን ሰርቆ ለሌቦች የሚልክ "Information Stealer" የተባለ አደገኛ ቫይረስ አብሮ ይጫናል።
🛠 ራሳችንን እንዴት እንጠብቅ? (3 ወርቃማ ህጎች)

1️⃣ "Sponsored" ወይም "Ad" የሚሉትን ሊንኮች ይለፉ፦ ጎግል ላይ ሰርች ሲያደርጉ ከመጀመሪያዎቹ 2 ወይም 3 ሊንኮች አጠገብ Sponsored የሚል ጽሁፍ ካዩ እሱን ይለፉት። ወደ ታች ወረድ ብለው ማስታወቂያ የሌለበትን ኦሪጅናል ሊንክ ይጫኑ።

2️⃣ የድረ-ገጹን ስም (Domain Name) በደንብ ያረጋግጡ፦ ሌቦች እውነተኛውን ስም በማስመስል ይጽፉታል። ለምሳሌ እውነተኛው
telegram.org ከሆነ፣ እነሱ telegram-download.org ወይም telgrem.org ሊሉ ይችላሉ። በፊደላት ጨዋታ እንዳይሸወዱ ስሙን ደግመው ያንቡ።

3️⃣ ከይፋዊ የApp Store ማውረድ፦ ከተቻለ ማንኛውንም አፕሊኬሽን ከጎግል ድረ-ገጽ ከመፈለግ ይልቅ በስልካችሁ ላይ ያለውን Google Play Store / App Store ወይም በኮምፒውተራችሁ ላይ ያለውን Microsoft Store በመጠቀም በቀጥታ አውርዱ።

የሳይበር ሌቦች ከቴክኖሎጂው እኩል ስልታቸውን እየቀየሩ ስለሆነ ሁልጊዜ በጥንቃቄ መፈለግን ልምድና አድርጉ! ይህንን መረጃ ለወዳጅዎ ሼር በማድረግ ከትልቅ ኪሳራ ይታደጓቸው። 🛡️

EthioCyebr
❤2
June 9, 2026 1.1K