𝐃𝐚𝐢𝐥𝐲 𝐡𝐚𝐝𝐢𝐭𝐡 ③⑥
══════◄••❀••►══════
🕌ጁሙዓ🕌
╚╩══• • •❀• • •══╩╝
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“#በጁምዓ ቀን በመስጂድ መግቢያ በር ላይ የሚቆሙና ሰዎችን ቅድሚያ በቅድሚያ (እንድአመጣጣቸው) የሚመዘግቡ መላዕክቶች አሉ። #በመጀመሪያው ሰዓት የመጣን ሰው #ግመል ሰደቃ እንዳቀረበ ይቆጠራል። ከዛ ቀጥሎ ባለው ግዜ የመጣ #በሬ እንዳቀረበ ይቆጠራል። ከዛ ቀጥሎ ባለው ግዜ የመጣ ሰው #በግ እንዳቀረበ ይቆጠራል። ከዛ ቀጥሎ ባለው ግዜ የመጣ ሰው #ዶሮ እንዳቀረበ ይቆጠራል። ከዛ ቀጥሎ ባለው ግዜ የመጣ ሰው #እንቁላል እንዳቀረበ ይቆጠራል። ከዛ ኢማሙ ለኹጥባ ሚንበር ላይ ሲወጣ መዝገባቸውን በመዝጋት ምክሩን ለማዳመጥ ይቀመጣሉ።”
📚 ቡኻሪ ዘግበውታል፡ 929
❢◥ ▬▬▬▬▬▬ ◆ ▬▬▬▬▬▬ ◤❢
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“#ጁምዓን በህብረት መስገድ ከአራት ሰዎች በስተቀር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። #ባሪያ፣ #ወይ_ሴትልጅ፣ ወይ #ህፃን ወይ #ህመምተኛ።”
📚 አቡ ዳውድ ዘግበውታል: 1067
❢◥ ▬▬▬▬▬▬ ◆ ▬▬▬▬▬▬ ◤❢
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
“#ኹጥባ ላይ ተገኙ፡፡ ወደ ኢማሙም ቅረቡ፡፡ አንድ ሰው ከኢማሙ ወደ ኋላ አይርቅም #ጀነትን ቢገባት እንኳን ከኋላ የሚደረግ ቢሆን እንጂ፡፡”
📚 ሰሂህ አልጃሚ: 200
❢◥ ▬▬▬▬▬▬ ◆ ▬▬▬▬▬▬ ◤❢
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿لَيَنْتَهينَّ أقْوامٌ عن ودْعِهِمُ الجُمُعاتِ، أوْ لَيَخْتِمَنَّ اللَّهُ على قُلُوبِهِمْ، ثُمَّ لَيَكونُنَّ مِنَ الغافِلِينَ.﴾
“#ህዝቦች የጁምዓ ሰላትን ከመተው ይከልክሉ። ወይም አላህ #በልቦቻቸው ላይ ያሽግባቸዋል። ከዚያም #ከዝንጉዎች ይሆናሉ።”
📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 865