በመካ መስጂደል ሐራም ውስጥ ሶላት በአንድ ኢማም ብቻ መስሰገድ ከጀመረ 100 ዓመት ደፈነ።
~
ለብዙ ክፍለ ዘመናትት በመካ ታላቁ መስጂድ ውስጥ ለአራቱ የፊቅህ መዝሃቦች የተለያዩ የሶላት ቦታዎች ነበሩ። የእያንዳንዱ መዝሃብ ተከታይም በራሱ ኢማም መዝሀብ ኢማም እየተመራ ነበር የሚሰግደው። አንድ ሶላት አራት ጊዜ ይሰገዳል ማለት ነው። ብዙውን ጊዜ የሻፊዒያ መዝሃብ ተከታዮች በመጀመሪያ ይሰግዱ ነበር፤ ከዚያም ሌሎቹ መዝሃቦች ተከታትለው ይሰግዱ ነበር። ይህም አንድ የሶላት ጊዜ በአንድ ቀን ውስጥ ብዙ ጊዜ እንዲደገም ያደርግ ነበር።
ንጉሥ ዐብዱልዐዚዝ - ረሒመሁላህ - እ.ኤ.አ. ጥቅምት 27 ቀን 1926 ይህ አሠራር እንዲቆም አዘዘ። ምሁራኑም ሁሉም ሙስሊሞች በአንድ ኢማም ሥር በአንድነት እንዲሰግዱ ተስማሙ። ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እያንዳንዱ ሶላት በአንድ ኢማም ብቻ አንድ የጀመዓ ሶላት ብቻ ይሰገዳል። በተለያዩ ኢማሞች የሚመሩ ተደጋጋሚ ጀመዓዎችም ሆኑ ለተለያዩ መዝሃቦች የተለዩ የሶላት ቦታዎች ሙሉ በሙሉ ተቋረጡ። ከነቢዩ ﷺ እና ሶሐቦቻቸው አሠራር ጋር የሚገጥመው ይሄኛው አካሄድ ነው። ሁሉም ሰጋጆች ከአንድ ኢማም በስተጀርባ በአንድነት ይቆማሉ፤ እንደ አንድ አካልም ይሰግዳሉ።
ይህ የንጉሥ ዐብዱልዐዚዝ ማስተካከያ ከተጀመረ ትናንት ማክሰኞ ኦክቶበር 27/2ዐ26 አንድ መቶ ዓመት ደፈነው። ዛሬ በመካ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች በአንድ ኢማም ሥር በአንድ ጀመዐህ ይሰግዳሉ።
እዚህ ሰፈር ሲዘዋወሩ ካገኘኋቸው ፅሁፎች ተወስዶ የተተረጎመ ነው።
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor
https://t.me/IbnuMunewor



