⸦የሶላት መማሪያ አፕ⸧
ሶላት የዲናችን ምሰሶ፣ የውስጥ ሰላማችን መገኛና በቀጥተኛው መንገድ ላይ ለመፅናት ከአላህ የተሰጠን ታላቅ ስጦታ ነው። ይህንን ታላቅ አምልኮ ደግሞ ነቢያችን (ﷺ) ባስተማሩንና በተገበሩት መንገድ መፈፀም ግዴታችን ነው።
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
"አሰጋገዴን አይታችሁ ስገዱ…" (ቡኻሪ ዘግበውታል)
ይህን ታላቅ መመሪያ በተግባር ለማዋልና የሶላት አፈጻጸማችንን ከነቢዩ (ﷺ) ሱና ጋር ፍጹም የተጣጣመ ለማድረግ የሚረዳ አጋዥ አፕ ይዘንላችሁ ቀርበናል!
ይህ መተግበሪያ ሶላትን ገና ከጅማሬው (ከአስገዳጅ ቅድመ-ሁኔታዎችና ከውዱእ) ጀምሮ እስከ ማጠቃለያው (እስከ ዚክርና ዱዓዎች) ድረስ ያለውን ሙሉ ሂደት እጅግ በቀላልና ግልጽ በሆነ መንገድ ያስተምራል። ጀማሪም ይሁን የሶላት አፈጻጸሙን ይበልጥ ማስተካከል ለፈለገ አካል፣ ይህ አፕ ተስማሚ ነው።
𑁍 የአፑ ዋና ዋና ጠቃሚ ባህሪያት፦
⌕ ደረጃ በደረጃ መመሪያ፡ እያንዳንዱን የሶላት እንቅስቃሴ (ሩኩዕ፣ ሱጁድ፣ ቂያም) ከትክክለኛ አቀማመጥ መግለጫዎች በምስል እና በድምፅ ከፅሁፍ ጋር ያብራራል።
⌕ የውዱእ አደራረግ ሥርዓት: ሶላት ከመጀመሩ በፊት የሚደረገውን የውዱእ አደራረግ በዝርዝር ያሳያል።
⌕ እያንዳንዱ ሂደት በነቢዩ (ﷺ) አስተማማኝ ሀዲሶች ላይ ተመስርቶ የተዘጋጀ ነው።
⌕ በየርዕሶቹ በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዋች እና መልሶቻቸው፣ በተጨማሪም የአጫጭር ሱራዋች ማብራሪያ።
⌕ ለማንበብ የሚስብ፣ ፈጣንና ቀለል ባለ ዲዛይን የተዋቀረ።
𑁍 ለምን "የሶላት መመሪያ" ያስፈልገናል?
ሶላትን በትክክለኛው መልክ መስገድ የዱንያም የኣኺራም ስኬት መረጋገጫ ነው። ይህ አፕ በተለይ፦
1. ሶላትን አዲስ ለጀመሩና ለሰለምቴዎች፣
2. በሶላት ውስጥ የሚባሉ ዚክሮችንና ዱዓዎችን በደንብ ማጥናት ለሚፈልጉ፣
3. የልጆቻቸውን ሶላት በሱና መሰረት ማረም ለሚሹ ወላጆች እጅግ በጣም ጠቃሚ ነው።
"ሶላታችንን ልክ እንደ ነቢያችን (ﷺ) አሰጋገድ በማሳመር የዱንያ ሰላምና የኣኺራ ስኬትን እንጎናጸፍ።"
📲 አሁኑኑ አውርደው ይጠቀሙበት! https://play.google.com/store/apps/details?id=com.salatguide.hudasoft.app
አፑን ለሌሎችም በማጋራት (Share በማድረግ) የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ! ጀዛኩሙላሁ ኸይረን።







