GLOW STAR SCHOOL 🌟 የወርሃዊ የሥራ ግምገማና የውይይት መርሃ ግብር የGlow Star School…

🌟 GLOW STAR SCHOOL 🌟
የወርሃዊ የሥራ ግምገማና የውይይት መርሃ ግብር

የGlow Star School አስተዳደር ከትምህርት ቤቱ ሠራተኞች ጋር የወርሃዊ የሥራ አፈጻጸም ግምገማና ሰፊ ውይይት አካሂዷል።

በውይይቱም የትምህርት ቤቱን አጠቃላይ አሠራር ማሻሻል፣ የመምህራንን የማስተማር ሂደትና የተማሪዎችን የመማር ውጤት ማሳደግ፣ ከወላጆች ጋር ያለውን ግንኙነትና ትብብር ማጠናከር እንዲሁም የተለያዩ የሥራ ክፍሎችን አፈጻጸም ማሻሻል በስፋት ተወያይተናል።

በተለይም ከአካዳሚክ፣ ከፋይናንስ፣ ከቤተ መጻሕፍት፣ ከትምህርት ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም ከሌሎች የትምህርት ቤቱ ክፍሎች ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር ገንቢ የሆነ ሐሳብ ልውውጥ ተደርጓል።
በውይይቱም ያሉ ጠንካራ ጎኖችን ማጠናከር፣ ያጋጠሙ ችግሮችን መለየትና መፍትሔ ማፈላለግ፣ ወደፊትም ሥራችንን በተሻለ ቅንጅት፣ በተጠያቂነትና በቁርጠኝነት ለመፈጸም የሚያስችሉ አቅጣጫዎች ላይ የጋራ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

የእኛ እምነት ግልጽ ነው፤ የተሻለ ትምህርት ቤት የሚገነባው በጋራ ውይይት፣ በትብብር፣ በተከታታይ ግምገማና በተግባራዊ ለውጥ ነው።

በጋራ እንወያያለን፤ በጋራ እንማራለን፤ በጋራ እናድጋለን!
November 3, 2026 798