የፈተና ውጤትህ/ሽ የሕይወትህ/ሽ መጨረሻ አይደለም!
ውድ ተማሪዎች ዛሬ የተሰማችሁ ብስጭትና ሀዘን ተፈጥሯዊ ነው። ብዙ ጊዜ ጠንክረህ ከሰራህ በኋላ ውጤቱ እንደጠበቅኸው ካልሆነ ልብህ ሊሰበር ይችላል።
💉 ነገር ግን አስታውስ....
አንድ ፈተና ብልህነትህን፣ ችሎታህን ወይም የወደፊት ዕድልህን አይወስንም።
➲ ይህ ውጤት ሽንፈት ሳይሆን፣ ያንተ ካልነበረው የተሳሳተ መንገድ ወጥተህ ራስህን የምትፈልግበት ሌላ እድል ነው።
➲ ዛሬ የወደቅክ ሊመስልህ ይችላል፤ ነገር ግን ከዚህ ቦታ ተነስተህ ነገ የሌሎችን ሕይወት የምትቀይር ሰው መሆን ትችላለህ።
የሚያሸንፉ ሰዎች ፈጽሞ የማይወድቁ አይደሉም፤ ከወደቁ በኋላ የሚነሱ ናቸው።
ይህን መልዕክት ምናልባት ዛሬ ተስፋ ለቆረጠ አንድ ተማሪ ሊደርስ ስለሚችል፣ ለጓደኞችህም አጋራው። 😊
ህይወት ይቀጥላል....
Telegram
Students channel
Stay will be Positive Attitude 😎

3
1August 27, 2026 102 2