Students channel: post #1840 — TG.ME

የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ምን አሉ ?

(የ2018 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት መግለጫ)

- የዘንድሮው ውጤት ከአምናው በጥሩ ደረጃ ተሻሽሏል።

- ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርስቲ አስገብቶ ማስፈተን በተጀመረበት የመጀመሪያ አመት ያለፉ 3.2% ፣ በሁለተኛው 2.9% ፣ በሶስተኛው 5.2% ፣ በአምናው አራተኛው ዓመት 8.9% ደረሰ አሁን በአምስተኛው ዓመት 12.8% ነው ያለፉት።

- ዘንድሮ በ2018 ብሔራዊ ፈተና የተመዘገበው ተማሪ ቁጥር 563,960 ሲሆን  550,210 ተማሪ ነው የተፈተነው።

- ፈተናውን ያለፈው ተማሪ ብዛት 70,544 ነው።

- ከተፈጥሮ ሳይንስ 16.6% አልፈዋል። ከማህበራዊ ሳንይስ 8.3% አልፈዋል።

#በፐርሰንት - ክልሎች ካስፈተኗቸው ተማሪዎች ምን ያህል ተማሪ አሳለፉ ? (ያሰፈተኗቸው ተማሪዎች ቁጥር ይለያያል)

1. አዲስ አበባ 32.3%
2. ሀረሪ 22.67%
3. አፋር 15.6%
4. አማራ 15.56%
5. ድሬዳዋ 11.29%
6. ትግራይ 11.2%
7. ኦሮሚያ 10.53%
8. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 9.23%
9. ሶማሌ 9.2%
10. ሲዳማ 6.95%
11. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 6.12%
12. ደቡብ ኢትዮጵያ 5.82%
13. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 4.92%
14. ጋምቤላ 3.74%

በቁጥር ምን ያህል ተማሪ ከየክልሉ አለፉ ? (ያስፈተኑት ቁጥር ይለያያል)

1. ኦሮሚያ 20,807 ተማሪዎች
2. አዲስ አበባ 18,646 ተማሪዎች
3. አማራ 15,225 ተማሪዎች
4. ትግራይ 3,146 ተማሪዎች
5. ደቡብ ኢትዮጵያ 3,011 ተማሪዎች
6. ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 2,800 ተማሪዎች
7. ሲዳማ 1,827 ተማሪዎች
8. ሶማሌ 1,616 ተማሪዎች
9. ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 835 ተማሪዎች
10. አፋር 705 ተማሪዎች
11. ሀረሪ 599 ተማሪዎች
12. ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 457 ተማሪዎች
13. ድሬዳዋ 410 ተማሪዎች
14. ጋምቤላ 280 ተማሪዎች

- ባለፈው ዓመት ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች 1,232 ነበሩ ዘንድሮ ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 565 ናቸው።

- ከዚህ ቀደም ምንም ተማሪ ካላሳለፉ ትምህርት ቤቶች ውስጥ በኮፒዩተር ፈተና ወደ 4,500 ተማሪዎች አልፈዋል።

ምንም ተማሪ ያላሳለፉ ትምህርት ቤቶች በክልል ምን ያህል ናቸው ?

• ኦሮሚያ 156
• አማራ 98
• ደቡብ ኢትዮጵያ 86
• ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 69
• ትግራይ 48
• ቤኒሻንጉል ጉሙዝ 29
• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 22
• አፋር 21
• ሲዳማ 16
• ሶማሌ 9
• ድሬዳዋ  5
• ሀረሪ 3
• ጋምቤላ 2
• አዲስ አበባ 1

- ሁሉንም ያስፈተኑትን ተማሪዎች ያሳለፉ 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ባለፈው አመት 62 ነበሩ ዘንድሮ 88 ሆነዋል።

በክልሎች ምንም ያህል ትምህርት ቤቶች 100% አሳለፉ ?

• ኦሮሚያ 37
• አዲስ አበባ 24
• አማራ 8
• ደቡብ ኢትዮጵያ 4
• ትግራይ 4
• ማዕከላዊ ኢትዮጵያ 3
• ሲዳማ 2
• አፋር 1
• ድሬዳዋ 1
• ሀረሪ 1
• ሶማሌ 1
• ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ 1

- በኮምፕዩተር እና በወረቀት በተፈተኑ ተማሪዎች መካከል ያለው የማለፍ ምጣኔ ትልቅ ልዩነት አለው። ኦንላይ የተፈተኑ 18.3% አልፈዋል። በወረቀት የወሰዱ 4.2% ናቸው ያለፉት። አንዱ ቶሎ በወረቀት ከመፈተን መውጥቶ ኦላይን ለመስጠት እቅድ አለው 60% ነው ዘንድሮ ቀጣይ አመት 100% ኦንላይን ሁሉንም።

- የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት ስንት ነው ?

በተፈጥሮ ሳይንስ
🥇 ከወንድ 👉 591/600 ኦዳ ስፔሻል ቦርንዲግ ትምህርት ቤት አዳማ
🥇 ከሴት 👉 583/600 ከአገው ምድር ትምህርት ቤት እንጅባራ

በማህበራዊ ሳንይንስ
🥇 ከወንድ 👉  576/600 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
🥇 ከሴት 👉 569/600 አዲስ አበባ ቦሌ ሱፐርሆሊሴቪየር ትምህርት ቤት

-  ስልክ ይዘው የገቡ 265 ተማሪዎች ከፈተናው ተሰርዘዋል።

- ኮምፒዩተር ላይ ባለ " ኢሬጉላተሪ " ተብለው ጉዳያቸው እየተጣራ ያለ አለ።

- ከዚህ በፊት ከነበረው መሻሻል እየታየ ስለሆነ በጣም ደስተኞች ነን።

- ዘንድሮም ወደ ሬሜዲያል የሚገቡ ተማሪዎች ይኖራሉ።

- ሬሜዲያል ሁሌ የሚኖር አይደለም። በሚያልፈው ተማሪ ብዛት ነው የሚወሰነው። ዘንድሮ 70 ሺህ ተማሪ ስላለፈ ዘንድሮ ሬሜዲያል የሚገባው ይቀንሳል።

📌 ተማሪዎች ውጤታቸውን ከነገ ሰኞ ወይም ከነገ ወዲያ ማክሰኞ ጀምሮ ውጤታቸው ማየት ይችላሉ። ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተማሪዎች ውጤት የሚመለከቱባቸውን አማራጮች ተከታትሎ ያቀርባል።

ነሐሴ 17 ቀን 2018 ዓ/ም
https://t.me/httpentra
Telegram
Students channel
Stay will be Positive Attitude 😎
August 23, 2026 163 1