የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ _______ የጤና ሚኒስቴር ነሀሴ 13-15 /2019 ዓ.ም ለሚሰጠው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ስማችሁን ከፋይዳ ቁጥር ጋር አያይዛችሁ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ሙያ ተመራቂዎች በሙሉ፤ ተመዛኞች ከሀምሌ 27- 30/2019 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ማስፈንጠሪያ /Link/ በመጫን FAYDA and Password በማስገባት የፈተና ጣቢያ እንድትመርጡ እናሳስባለን፡፡ ማሳሰቢያ፦ ▪ እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት የፈተና ጣቢያ ምርጫ ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን። ▪ በምዝገባ ወቅት ለሚገጥማችሁ ማንኛውም ችግር በነጻ የስልክ መስመር 952 በመደወል ከዚያም 3 ቁጥርን በመጫን በቀጥታ እገዛ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን፡፡ Website: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6
የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ _______ የጤና ሚኒስቴር ነሀሴ 13-15 /2019… — Authentication of Educational Credentials — TG.ME
August 3, 2026 5.7K 59