ETA የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 ላይ… — Authentication of Educational Credentials — TG.ME

#ETA የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 ላይ ያደረጋቸው ማሻሻያዎች ምን ይላሉ? ባለሥልጣኑ በመመሪያው አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ ማሻሻያዎች ያደረገ ሲሆን፤ በረቂቅ ማሻሻያዎቹ ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት እስከ ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም አስተያየታቸውን እንዲሰጡ መጠየቁ ይታወቃል። ማሻሻያዎቹ፦ በቀድሞው ዲፕሎማ / ከ12+2 /ከ10+3 ወይም ከቴክኒክና ሙያ ደረጃ አራት ስልጠና ተመርቀው ያጠናቀቁ ትክክለኛነቱ በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ወይም በፌደራል ወይም በክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም የተረጋገጠ ኦሪጅናል የስልጠና ማስረጃ ወይም ዲፕሎማ እና ትራንስክሪፕት ኖራቸው ነገር ግን የደረጃ አራት የብቃት ማዕቀፍ ሳይኖራቸው በመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው የተመረቁ የትምህርት ማስረጃ የሚረጋገጥላቸው፦ ሀ) ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ይህ መመሪያ እስከተሻሻለበት ጊዜ የተመረቁ እና የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፋ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል፡፡ ለ) ሆኖም ከላይ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ ፩ (ሀ) የተጠቀሰው ቢኖርም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ የያዙ ባሉበት የትምህርት ደረጃ (BA, MA, and PhD) ላይ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው በያዙት የትምህርት ደረጃ ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል። ሐ) ይህ መመረያ ተሻሽሎ በስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ያለበት ትምህርት ሚኒስቴር ወይም ማንኛውም የሚመሰከተው አካል የሚያወጣውን የመግቢያ መስፈርት ብቻ ተከትሎ ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር አለበት። በማሻሻያዎቹ ላይ አስተያየት ይስጡ 👇 https://forms.gle/ndRhodE2yoHSn2P5A ሊንኩን በመጫን አስተያየት መስጫውን ማግኘት ትችላላችሁ፤ አስተያየታችሁን ሞልታችሁ ስትጨርሱ Submit የሚለውን በመጫን አስተያየታችሁን ይላኩ። በተጨማሪ ለሚኖራችሁ ማንኛውም አስተያየት በባለሥልጣኑ ኢ-ሜይል አድራሻ [email protected] ላይ አስተያየታችሁን ሞልታችሁ መላክ ትችላላችሁ ተብሏል። @tikvahuniversity

July 13, 2026 9.2K 74