የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለወሰዳችሁ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ _______ በሰኔ 2018 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር… — Authentication of Educational Credentials — TG.ME

የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለወሰዳችሁ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ _______ በሰኔ 2018 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር በኩል የተሰጠውን የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና የወሰዳችሁ ተመዛኞች ከሰኔ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ https://hple.moh.gov.et ላይ በመግባትና የብሄራዊ መለያ ቁጥር(FAN) እና Password በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ውጤት ከተገለጸበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት በስልክ ቁጥር 952 በስራ ሰዓት በመደወል ሙሉ ስም፣ ዲፓርትመንት እና የተማራችሁበትን የትምህርት ተቋም ስም በማሳወቅ ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ ማሳሰቢያ፦ የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከሰኞ ሃምሌ 6/2018 ዓ.ም ጀምሮ ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል የሚላክ ስለሆነ የሙያ ፍቃዳችሁን 12ተኛ ክፍል በተማራችሁበት ክልል ማውጣት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ Website: moh.gov.et Facebook: Ministry of Health,Ethiopia Twitter: x.com/fmohealth YouTube: youtube.com/@FMoHealthEthiopia Tiktok: tiktok.com/@mohethiopia Telegram: t.me/M0H_EThiopia Linkedin: lnkd.in/ewFJ6VA

July 3, 2026 8.5K 41