ቀን ሰኔ 29/2018ዓ.ም
"እንኳን ደስ አላችሁ"
ለሀሌሉያ ቅድመ አንደኛ፣አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
አጠቃላይ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞች፣ወላጆች እና ለትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ በሙሉ ትምህርት ቤታችን በ2018ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ6ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ማስፈተኑ ይታወቃል። በመሆኑም ት/ቤቱ ካስፈተናቸው 107 ተማሪዎች ሁሉንም ተማሪዎችን ወደ 7ኛ ክፍል በማሳለፍ እና 100% አፈፃፀም በማስመዝገቡ እንኳን ደስ አለን /አላችሁ/ እያልኩ
ለዚህ ውጤት መሳካት ከፍተኛ ርብርብ ስታደርጉ የነበራችሁ የትምህርት ቤታችን የትምህርት አመራሮች፣የት/ቤታችን ትጉ መምህራን ፣አስተዳደር ሠራተኞች፣
የት/ቤቱ የወተመህ ስራ አስፈፃሚዎች እንዲሁም የክላስተር ሱፐርቫይዘሮች ለነበራችሁ ድጋፍና ሁለንተናዊ ትብብር በት/ቤታችን ስም ከልብ እናመሰግናለን።
በድጋሜ እንኳን ደስ አላችሁ!!!"















