🎡🎡🎡🛝🛝🎡🎡🎡 ሆራይዘን አካዳሚ ለውድ የሆራይዘን አካዳሚ ማህበረሰቦች፡- ቢያሰፈልጎት 🔊 ⚠️አንድ ልጅ የቋንቋ/ንግግር እድገቱ ዘገየ ሕክምና ይፈልጋል የሚባለው መቼ ነው❓️ 🔊 15ወር(አንድ ዓመት ከ3 ወር) ላይ ⚠️ ዕቃዎችን የማያመለክቱ ከሆነ(lack of pointing) ⚠️ ለስማቸው ምንም አይነት ምላሽ የማይሰጡ ከሆነ ⚠️ የሚፈልጉትን ነገር ለመጠየቅ ወይም ለመጫወት ወደ ወላጆች ወይም ወደ ሌሎች ሰዎች ጋር የማይሄዱ ከሆነ ⚠️ ቢያንስ 3 ቃላትን የማይጠቀሙ ከሆነ 🔊 18ወር(አንድ ዓመት ከ 6 ወር ) ላይ ⚠️ ቀላል መመሪያዎችን/ትእዛዞችን የማይከተሉ ከሆነ (ለምሳሌ ኳሱን አምጡ ሲባሉ የማይሰሙ የማያመጡ ከሆነ ) ⚠️ ማማ፣ ባባ ወይም ሌሎች ስሞችን አለመጠቀም ካለ ⚠️ ተደጋጋሚ ነገሮችን/እንቅስቃማድረግ 🔊 ሁለት ዓመት(24 ወር)ላይ 👇 ⚠️ ስዕሎችን ወይም የአካል ክፍሎችን የማያመለክቱ ከሆነ ⚠️ 25 ቃላትን መጠቀም ካልቻሉ ⚠️ አይን ቀና ብለው የማያዩ ከሆነ ⚠️ ከሌሎች ህፃናት ጋር መጫወት የማይችሉ ከሆነ 🔊 ሶስት ዓመት ላይ ⚠️ ተመሳሳይ ቃል የሚደጋግሙ ከሆነ ⚠️ ተመሳሳይ እና ተደጋጋሚ መጫወቻዎችን የሚጠቀሙ ከሆነ ⚠️ ለብቻ መሆንን የሚመርጡ ከሆነ ⚠️ ለጥያቄዎች በቃል መልስ የማይሰጡ ወይም ጭንቅታቸውን የማያነቃንቁ ከሆነ 2-ቃል ሀረጎችን እየተጠቀሙ ካልሆነ 🔊 አራት ዓመት ላይ ⚠️ ባለ 2- step መመሪያዎችን መከተል አለመቻል ካለ (ለምሳሌ ኳሱን ከመሬት አንስተህ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው) ⚠️ ከ200 ያነሱ ቃላቶችን ብቻ የሚያውቁ ከሆነ ⚠️ ነገሮችን የማይጠይቁ ከሆነ; ⚠️ ሲጠየቁ ጥያቄውን ከመመለስ ይልቅ ጥያቄውን የሚደግሙ ከሆነ(Echolalia) ⚠️ 2-ቃል እያገናኘ መናገር ከጀመረ በኃላ ማፈግፈግ( መናገር መተው) 🔊 ከላይ በተጠቀሰው እድሜ ስር የተዘረዘሩትን የቋንቋ ችግሮች በልጆች ላይ ከተመለከቱ የህፃናት ስፔሻልስት ሀኪም ጋር ቀርበው ቢማከሩ እና ቢያሳክሙ መልካም ነው፡፡ 👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇 የጠቢብነት ማዕከል!! 📞 0118-463631 ☎️ 0913-000055 ☎️ 0966-706126
ሆራይዘን አካዳሚ ለውድ የሆራይዘን አካዳሚ ማህበረሰቦች፡- ቢያሰፈልጎት 🔊 ⚠️አንድ ልጅ የቋንቋ/ንግግር… — Horizon Academy Ethiopia 🇪🇹/ሆራይዘን አካዳሚ ..አ.አ...ኢትዮጰያ 🇪🇹official — TG.ME
September 4, 2026 271 2 1