ሆራይዘን አካዳሚ Horizon Academy በድጋሚ በሆራይዘን አካዳሚ ለቅድመ አንደኛ(ኬጂ) ነባርና አዲስ… — Horizon Academy Ethiopia 🇪🇹/ሆራይዘን አካዳሚ ..አ.አ...ኢትዮጰያ 🇪🇹official — TG.ME

ሆራይዘን አካዳሚ                   Horizon Academy በድጋሚ በሆራይዘን አካዳሚ ለቅድመ አንደኛ(ኬጂ) ነባርና አዲስ ተማሪዎች በሙሉ ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የአንደኛ ዙር መማሪያ መፅሐፍ ለመግዛት ብር ያስገባችሁ እና ያልከፈላችሁ ለሁላችሁም የተማሪ ወላጆች የመማሪያ መፅሐፍ የመጣላችሁ ሲሆን ከሰኞ ነሀሴ 25/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘውትር በስራ ቀን ከ2:00 እስከ 7:00 ሰዓት ድረስ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ በመያዝ ትምህርት ቤት በመምጣት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን ለማሳወቅ እንወዳለን። 👉የአንደኛ ደረጃ(1-8ክፍል) ተማሪዎች የመማሪያ መፅሐፋ ተሟልቶ እንደመጣ የምቶሰዱበትን ቀን በዚሁ ቴሌግራም ገፃችን ላይ የምናሳውቃችሁ ይሆናል። ትምህርት ከጀመረ በኃላ የሚመጣ ማንኛውም የተማሪዎቻችንን ወላጅ የማናስተናግድ መሆኑን እናሳውቃለን። 👉 ለ2019 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ቤታችን በሆራይዘን አካዳሚ ትምህርታችሁን ለመከታተል ወስናችሁ ለተመዘገባችሁ በሙሉ ከወዲሁ መልካም የትምህርት ዘመን እንመኛለን። አካዳሚው!

August 31, 2026 455 1