╔══❖•🦜🦜🦜•❖══╗ ♥♥የመረረ ፍቅር♥♥ ክፍል ሁለት እውነተኛ ታሪክ ╚══❖•🦜🦜🦜•❖══╝ . . . የፈጣሪ ያለህ የዚህን ያህል መርበትበት ምን ይሉታል ብዬ ቀልቤን ሰበሰብኩና አሁን ተሽሎኛል መውጣት እንችላለን አልኳቸው። ዛክ ከተቀመጠበት ተነስቶ አይ መቆየት አለብህ እመለሳለው ብሎ ወጣ ሁለቱ ሴቶች እና እኔ ብቻ ቀረን ለኔ ቤልገባኝ ቋንቋ ይፍነከነካሉ ባይገባኝም አብሬ መሳቅ ጀመርኩ በመሀል የሙና ስልክ ጠራ ሙና ስልክ ለማናገር ወጣች ሠሊና እና እኔ አንድ ክፍል ብቻችንን ቀረን ደስ ይላል.. ሠሊና እኔን ከመተያየት ያለፈ የሚያግባባን ምክኒያት ጠፋ በመሀል አፌ እንደ ህፃን ልጅ እየተኮላተፈ ማማ ማን ማን ነበር ስምሽ አልኳት ፈገግ አለችና መርሳት አጋጠመህ እንዴ ሰሊና አለችኝ እኔም ስታወራ የምታወራውን ሳይሆን ከንፈሯ ሲላወስ ጉንጮቿ ትርክ ትርክ ስርጉድ ሲሉ እየተመለከትኩ ወሬዋ ባላለቀ ሌላ ወሬ በጀመረች እያልኩ ሳስብ ሙና በሩን ከፍታ ገባች እና በፍጥነት ቦርሳዋን አንስታ ጋይስ ቻው እመለሳለው ብላ ቅብጥ ቅብጥ እያለች ወጣች። አሁን የሚያሰጋኝ ነገር የለም ከ ሰሊና ጋ ብቻችንን ቀረን ጨዋታ መጀመር አለብኝ አልኩና በመሀል ምንም የህመም ስሜት ሳይሰማኝ እእእእእ ወገቤ ብዬ ጮውኩኝ ሰሊና ተደናግጣ ምነው ምን ሆንክ አለችና ወደኔ ተጠጋች ወገቤን አመመኝ ሰሊና አልኳት በድንጋጤ ዶክተሩን ልጥራው አለችኝ እኔም በድፍረት አይ አያስፈልግም ባይሆን ወገቤን,,,,,, አላስጨረሰችኝም በፍጥነት አልችልበትም ግን ከተሻለህ ልሞክር አለችና በደረቴ እንድጋለል በአይኗ አዘዘችኝ እንዳዘዘችኝ አደረኩ እንደ አለንጋ እጥፍ ዝርግት የሚሉ ጣቶቿን ወገቤ ላይ ስታንሸረሽራቸው እንኳንስ ያልታመመው ወገቤ የታመመው እግሬም የህመም ስሜት አይሰማውም ነበር ደነዘዝኩ በቃ። እጇ መድሀኒት ነው ልክ እንደ እትዬ አሰፉ እትዬ አሰፉ የሠፈራችን ምርጥና ተወዳጅ የባህል ሀኪም ነበሩ እትዬ አሰፉ እንኳንስ የነካችው እግዜር ይማርህ ያለችው ሰው ይድናል ይባል ነበር። እኔም ወደ ሠሊና ቀና ብዬ ልክ እንደ እትዬ አሰፉ ነሽ ሰሊና እየተሻለኝ ነው አልኳት ፈገግ አለችና እትዬ አሰፉ ማናቸው አለችኝ ደስ እያለኝ የሠፈራችን ሀኪም አልኳት ከት ብላ ሳቀች እኔም ተከትያት ሳኩኝ ክላሡ በሁካታ ተሞላ ይህንን የሠማ አንድ ታካሚ በር ላይ ቆመና ሲመለከተን ቆየና በድንገት "ፍቅራችሁ ያስቀናል ያርዝምላችሁ ደስ ስትሉ አለን"ሰሊና እና እኔ በሽቅድምድሞሽ እኔ ኧረ ፍቅረኛሞች አይደለንም እሷ ደግሞ እናመሠግናለን አለችና ፈገግ አለች እኔ ግራ ገባኝ ብቻ ሰሊና ጣጣ የሌለባት መሆኗን ሳውቅ ይበልጥ ልቤ መምታት ጀመረ እሷም ከጎኔ እንደቆመች እኔም ከሷ ላይ አይኔን እንደተከልኩኝ ዛክ በሩን ከፍቶ ገባ። ዛክ በፌስታል ሙዝ እና ብርቱካን ይዟል እንዴት ቆየህ ጓደኛዬ ሰሊና ስታደርቅህ ቆየች አይደል ብሎ ከፌስታሉ ሙዝ አውጥቶ ሰጠኝ እና በል ብላ ብሎ ለነሡም አንድ አንድ አንስተው ወሪያችንን ቀጠል ከሆስፒታል መውጣት እስኪያስጠላኝ ድረስ ሆስፒታል መሆናችንን ወድጀው እያለ ዶክተሩ መውጣት እንዳለብን ነገረን ተያይዘን ወጣን። እኔም ሰሊናን እንደተለየው ጭንቅላቴ ዞረ ዳግም የማላገኛት መሠለኝ ነገር ግን ለሷ ያለኝ ስሜት እየጨመረ ቢሄድም በቀን በቀን እየተገናኘን መጫወት አዘወተርን አራታችንም ደስ የሚሉ ቀናቶችን እያሳለፍን አንድ ቀን ለመዝናናት ወተን የጭርቃት ኳስ ስንጫወት ሙና እና እኔ በአንድ ዛክ እና ሰሊና በአንድ ሁነን ተጋጠምን የተሸነፈ ሊጋብዝ ያሸነፈ ሊጋበዝ ነበርና ጨዋታችን የደራ ነበር በጨዋታ እንበልጣቸዋለን እኛ ግን አልተናበብንም ነበር እና አሸነፉን ከዛ እርስ በርሳችን ስንፎጋገር ሙና ስማማ መልክዬ አለችኝ እህ አልኳት ከንፈሯን በእጇ እየዳሰሰች ዛክ እና ሰሊና እኮ ስትለኝ ላስጨርሳት አልቻልኩም ደነገጥኩኝ ልቤን ፍርሀት ተሰማው ቢሆንም ግን ቁርጤን ለማወቅ እሽ!! ዛክና ሰሊና ምን..? አልኳት። . ...☞ይቀጥላል . . . በቶሎ እንዲቀጥል LIKE👍 እና ኮመንት ላይ p3 ብቻ ይፃፉ😘 . . ╔══❖•🍀🌼🌺•❖══╗ LIKE SHARE COMMENT ╚══❖•🍀🌼🌺•❖══╝ . . . Hagerefic የቴሌግራም ቻናል 𝐉𝐨𝐢𝐧 በማለት ራሶን በጣፋጭ ትረካዎች ዘና ያድርጉ ..♥️✨ . . .............................. . 𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/hagerefic https://t.me/hagerefic ╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
TelegramHagere~fic🇪🇹 ወደ ቻናላችን እንኳን በሰላም መጡ 🇪🇹 ✒️በዚህ ቻናል ውስጥ ✦ ጠቃሚና አስተማሪ የሆኑ ጽሁፎች የሚለቀቁበት 📖 🎀 ደስ የሚሉ አስተማሪ ምክሮች ባጠቃላይ ሁሉንም አዘል የምታገኙበት ቻናል ነው📚 📢ቻናላችንን share በማድረግ ተባበሩን🙏የመረረ ፍቅር♥♥ ክፍል ሁለት እውነተኛ ታሪክ ╚══❖•🦜🦜🦜•❖══╝ . . . የፈጣሪ ያለህ የዚህን ያህል… — Hagere~fic — TG.ME
August 9, 2025 101