╔══❖•🦜🦜🦜•❖══╗ ♥♥የመረረ ፍቅር♥♥ ክፍል አንድ እውነተኛ ታሪክ ╚══❖•🦜🦜🦜•❖══╝ . . . ተወልጄ ያደኩት በውቧ በደሴ ከተማ ነው ደሴ ላይ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ከተማርኩ በኋላ የኢንትራንስ ውጤቴ አሪፍ ስለነበር መቀሌ ዩኒቨርስቲ በጋዜጠኝነት የትምህርት ዘርፍ ሁለት ሺህ ስምንት ላይ መቀሌ ዩኒቨርስቲን ተቀላቀልኩ መቀሌን በስምንት ቀን ውስጥ ለመድኳት ብዙ ጓድኞችን ተዋወኩ የመጀመሪያውና ለኔ ለዘላለም ከልቤ ላይ ነግሶ የሚኖረው ጓድኛዬ ዘካሪያስ ይባላል የመቀሌ ልጅ ነው። እንደ ዘካሪያስ ያለ ጓድኛ ማግኘት ቢከብድም ለኔ ግን ሰቶኛል ዛክ ጋ በቶሎ ተግባባን አብረን መዋል አብረን ማንበብ አብረን መዝናናት የቀን ተቀን ስራችን ሆነ። አገሩን በደንብ አስጎበኘኝ ጓድኝነታችን ከጓድኝነት አልፎ ወደ ወንድማማችነት ተለወጠ እኔም የወንድሜን ያህል ወደድኩት እሱም እንደኔው ቀኑን በውል ባላቀውም ህዳር ወር ላይ ዛክ የሴት ጓድኞቹን ሊያስተዋውቀኝ ካፌ ተቀጣጠርን እኔም ሴቶች ጋ ስገናኝ የመጀመሪያዬ ነውና አለባበሴን አሳምሬ ወደ ተቀጣጠርንበት ካፌ ከነፍኩኝ ከካፌው በር ላይ ቁሜ ስመለከት ዛክን አየሁት እሱም እኔን ፍለጋ አይኑን ከወዲያ ወዲህ ሲያቅበዘብዝ ተመለከትኩት። ረጋ ባለ አረማመድ ወደ እነ ዛክ ስሄድ በድጋሜ አይኔን ከጎኑ ካሉት እንስቶች ላይ ጣልኩት። ወደኔ የዞረችዋ ጉብል አይኗ እንደ ሠማይ ክዋክብት ያበራል ፀጉራ በወገቧ ተግለስልሶ ወርዷል ልክ ሳያት ልቤ መታ ሰውነቴ ዛለ ሰውነቴን የሆነ የማላቀው አዲስ ስሜት ወረረኝ መራመዴን ረስቼ እሷን ስመለከት መንገዴ ላይ የነበረ ወንበር አደናቅፎኝ በቁሜ ተዘረርኩኝ እንደምንም አቃትቼ ለመነሳት ስመሞክር መነሳት አልቻልኩም በደቂቃ ውስጥ መውደቄን የተመለከተ የካፌው ተጠቃሚ ሰው ሁሉ ከበበኝ ይበልጥ አመመኝ በአይኔ የማውቀው ሰው አጥቼ ስፈልግ ዛክ ዘሎ ተከመረብኝ ይርበተበታል ደህና ነኝ ጓድኛዬ ተረጋጋ አልኩትና ለመነሣት ያለ የለለ ኃይሌን ተጠቅሜ ስንጠራራ የማላቀው ሰው ሊያግዘኝ እጄን ያዘኝ ወደ ላይ ቀና ስል ዳግም መውደቅን ተመኘሁ ያየሁትን ሰው ማመን አቃተኝ። ዳግም መውደቅን ተመኘሁ አለንጋ የመሰሉ ጣቶቿ ከጄ መዳፍ ላይ ሲንሸረሸሩ ደስ የሚል ስቃይ ተሰማኝ እሷ ባለችበት ሁሉ መውደቅን ተመኘሁ ሰዉነቴ መርበትበት ጀመረ ህመሜን ረሳሁት እጆቿን ከእጆቼ መለየት አልፈለኩም እጆቿን ጠበቅ አድርጌ ይዠ ተነሳሁ አካሌ የኔ አልመስልህ አለኝ የኔን መውደቅ ለመመልከት ዙሪያዬን የከበበኝ ሰው አዲስ አበባ ስታድየም የቡና እና የጊዮርጊስ ጨዋታ ለመታደም የመጣ ያህል ነበር ከህመሜ በላይ የሠውን አይን ፈራሁት ከቆምኩበት ሆኜ ዙሪያየን ስመለከት አይኔ ፈዘዘ ዛክ በል ተራመድ እስኪ አይዞህ አለኝ እሺ ብዬ ለመራመድ ስሞክር አልቻልኩምና ወደ ዛክ ዞር ብየ አልቻልኩም ጓድኛዬ አልኩት ስሟን ገና ያላወኳት ግን በደቂቃ እይታ በፍቅር የወደኩላት እንስት ልደግፍህ አለችኝና እጄን ሳብ አድርጋ ትከሻዋ ላይ አደረገችው አሁንም ሌላ ስሜት ወረረኝ የሆነ ደስ የሚል በስቃይ የተሞላ ደስታ ከዛማ እኔስ ህመምተኛ አይደለሁ ተጠመጠምኩባት እንደምንም ተገፋፍተን ከካፌው ወጣን ዛክ ላዳ ታክሲ ፈለገ እና ወደ ሆስፒታል ሄድን ሆስፒታል ስደርስ ግን ከበፊቱ ተሻለኝ እያነከስኩም ቢሆን መራመድ እችል ነበር ነገር ግን አሁንም መታቀፍ አማረኝ ያውም በቆንጆና በምወዳት ሴት እቅፍ ዛክ ከኛ ቀድሞ ወደ ካርድ ክፍል ሮጠ እኔም በዛክ ጓድኞች ተከብቤ ወደ ሆስፒታል ገባን ከቆይታ በኋላ ዶክተሩ ትንሽ እረፍት ያስፈልገዋል ስላለኝ አልጋ ያስኩኝ ዛክም ተረጋግቷል ጓድኞቼን ተዋወቃቸው አለኝ። በመጀመሪያ ፀይም ዘለግ ያለች ቆንጆ ሙና እባላለሁ አለችኝ ሁለተኛዋ እኔ ልቤ በደቂቃ ውስጥ በፍቅር የከነፍኩላት ባለዞማ ፀጉር መልኳ የቀይ ዳማ ዘለግ ያለች ቆንጆ አተኩራ እያየችኝ እጇን ዘረጋችና....ሰሊና እባላለሁ ስትለኝ እጄን ዘርግቼ ቀረሁኝ አንደበቴ ዲዳ ሆነ በርጋታ መልክየ እባላለሁ አልኳት። . ...☞ይቀጥላል . . . በቶሎ እንዲቀጥል LIKE👍 እና ኮመንት ላይ p2 ብቻ ይፃፉ😘 . . ╔══❖•🍀🌼🌺•❖══╗ LIKE SHARE COMMENT ╚══❖•🍀🌼🌺•❖══╝ . . . Hagerefic የቴሌግራም ቻናል 𝐉𝐨𝐢𝐧 በማለት ራሶን በጣፋጭ ትረካዎች ዘና ያድርጉ ..♥️✨ . . .............................. . 𝗝𝗼𝗶𝗻 𝘂𝘀 ╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗ ♥️♥️ተቀላቀሉን ♥️♥️ https://t.me/hagerefic https://t.me/hagerefic ╚═══❖•🌺🌸•❖═══
TelegramHagere~fic🇪🇹 ወደ ቻናላችን እንኳን በሰላም መጡ 🇪🇹 ✒️በዚህ ቻናል ውስጥ ✦ ጠቃሚና አስተማሪ የሆኑ ጽሁፎች የሚለቀቁበት 📖 🎀 ደስ የሚሉ አስተማሪ ምክሮች ባጠቃላይ ሁሉንም አዘል የምታገኙበት ቻናል ነው📚 📢ቻናላችንን share በማድረግ ተባበሩን🙏የመረረ ፍቅር♥♥ ክፍል አንድ እውነተኛ ታሪክ ╚══❖•🦜🦜🦜•❖══╝ . . . ተወልጄ ያደኩት በውቧ በደሴ… — Hagere~fic — TG.ME
August 8, 2025 88