የበረሃ እንባ 💔 [ የሊብያ በርሃ ] ​ክፍል 6 ​ፀሐፊ zoya~ ......​ኦርሳም በተጫነባት የጭነት… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

የበረሃ እንባ 💔 [ የሊብያ በርሃ ]

​ክፍል 6

​ፀሐፊ zoya~

......​ኦርሳም በተጫነባት የጭነት መኪና ላይ ሆኖ አንገቱን አዙሮ ወደ ኋላ ተመለከተ የኢዘዲን መኪና ወደ ሌላ አቅጣጫ እየራቀች በካርቱም አቧራ ውስጥ ተዋጠች ያ የለመደው የሚያበረታታውና አይዞህ የሚለው ወንድሙ ከጎኑ የለም አሁን ያለው እሱ አራት የማይውቃቸው የሶማሌ ወጣቶችና መሳሪያ የያዙ ሁለት ጋርዶች ናቸው ግን ኦርሳም ደላሎቹን አተኩሮ ያያቸዋል ጥርጣሬው የሱዳን ሰዎች አይመስሉም ።

​መኪናዋ ከተማዋን ጥላ ወደ በረሃማው ዳርቻ ስትነጉድ የድንጋይ ከሰል ማምረቻው ድምፅ ከሩቅ መሰማት ጀመረ ጥቁር ጭስ ሰማዩን ውጦታል ኦርሳም እጆቹን አየት አደረጋቸው ገና ሳይጀምረው መዛል ጀምረዋል  በውስጡ ግን "እማ... ሀኪያ... ለእናንተ ስል እቆማለሁ" እያለ ራሱን ያበረታታል ።

​በክሊኒኩ ውስጥ የነበረው ፀጥታ በሀኪያ ድንገተኛ ሳል ተሰበረ ወይዘሮ ጀሚላ  ደንግጠው ተነሱ ሀኪያ አይኖቿን በጭንቅ ከፍታ እናቷን ተመለከተች  "እማ... ዛሬ ስንት ቀኑ ነው?" አለች ድምጿ እየተቆራረጠ
​ወይዘሮ ጀሚላ ግንባሯን እየሳሙ " ሶስት ሳምንት ሳምንት አለፈው ልጄ... ግን አይዞሽ ጎረቤቶች ሁሉ ዱአ እያደረጉ ነው" አሏት። ወይዘሮ ጀሚላ የልጃቸውን ሁኔታ እያዩ በውስጣቸው የሚቃጠለውን እሳት ደብቀውታል ኦርሳም በሄደ በሳምንቱ የቤቱ ኪራይ ደርሷል የቀለብ ነገር ደግሞ ሌላ ራስ ምታት ሆኗል።
​"ኦሪ... የት ነህ ልጄ? በላህ ወይ? ጠጣህ ወይ?" እያሉ በልባቸው ይጮኻሉ ያቺ ደብዳቤ አሁንም ከደረታቸው አልተለየችም።


​ኦርሳም ከመኪናው እንደወረደ የደረሰበት ንዳድና የከሰሉ ሽታ ትንፋሽ አሳጣው አንድ ግዙፍ ሱዳናዊ ደላላ ወደ እሱ መጥቶ በትልቅ አካፋ መሬቱን መታ።
​"اسمع! العمل يبدأ الآن!

"ስማ ስራው አሁን ይጀምራል!" እያለ ጮኸበት።

​ኦርሳም ምንም አልገባውም ዝም ብሎ ሲያየው ደላላው በትከሻው ላይ ያለውን ሸራ ገፍቶ በትልቅ አካፋ ከሰል እንዲጭን ምልክት ሰጠው።
"ይሄን ሁሉ?" አለ ኦርሳም ወደ ተከመረው ጥቁር ተራራ እያየ ለስድስት ወራት የሚቆየው ስቃይ የመጀመሪያው ሰዓት ተጀመረ
​አካፋው በእጁ ላይ ሲያርፍ እንደ እሳት ይለበልበዋል ገና አስር አካፋ ሳይጭን እጆቹ አበጡ ። ፀሐይዋ ጭንቅላቱ ላይ የቆመች ትመስላለች በየአምስት ደቂቃው ውሃ እያለ ቢለምንም  ዘበኞቹ ግን በንቀት "በኋላ " በሚል ምልክት ያባርሩታል።

​ኢዘዲን የደረሰበት እርሻ በጣም ሰፊ ነው እሱ የተመደበው ትላልቅ የውሃ ቱቦዎችን እየተሸከመ መስኖ ማስተካከል ላይ ነው ስራው ከእርሻ ይልቅ የግንባታ ስራ ይመስላል ኢዘዲን ግን አእምሮው ያለው ኦርሳም ጋር ነው
​"ኦሪ... ምስኪኑ ወንድሜ ይሄን ስራ እንዴት ይቋቋመው ይሆን?" እያለ ይጨነቃል አጠገቡ ካለ አንድ ሶማሊያዊ ወጣት ጋር በምልክት ለማውራት ሞከረ።
​"ካርቱም... ፎን (ስልክ)?" አለው።
ሶማሊያዊው ግን ራሱን በመነቅነቅ
"ኖ ፎን... ኦንሊ ወርክ (ስልክ የለም... ስራ ብቻ)" አለው። ኢዘዲን ተስፋ መቁረጥ ወረረው ስድስት ወር ሙሉ ያለ ድምፅ ያለ መረጃ መኖር መቃብር ውስጥ እንደመኖር ተሰማው።

​ምሽቱ ላይ
​በከሰል ማምረቻው ውስጥ ኦርሳም ስራውን ጨርሶ መሬት ላይ ተዘረረ ፊቱ፣ ልብሱ፣ ጥፍሮቹ ሁሉ በጥቁር ከሰል ተለውጠዋል። የሚጠጣው ውሃ እንዲሰጡት ሲለምን አንድ የቆሸሸ ባልዲ ውሃ አመጡለት ውሃው ውስጥ ትናንሽ ነፍሳት ይታያሉ ግን ጥሙ የገደለው ኦርሳም አይኑን ጨፍኖ ጠጣው

​ለሊቱን የሚያሳልፉት በአንድ አሮጌ ድንኳን ውስጥ ተጨናንቀው ነው ኦርሳም በዚያ ድቅድቅ ጨለማ ውስጥ ሆኖ የሀኪያን ሳቅ አሰበ "ሀኩ... የኔ አበባ፣ ለዚህ ነው እኮ ጥዬሽ የወጣሁት በረሃው ቢበላኝም አንቺ መዳን አለብሽ" እያለ በሹክሹክታ ለራሱ ይናገራል።
​በድንገት ከመጋዘኑ ውጭ የተኩስ ድምፅ ተሰማ ሁሉም ደንግጠው ሲነሱ ዘበኞቹ በየቋንቋቸው ይጮኻሉ ኦርሳም ልቡ መምታት ጀመረች"ምን ተፈጠረ?" ብሎ በድንጋጤ ሲያይ ደላሎቹ አንዱን ለማምለጥ የሞከረ ወጣት እየጎተቱ ወደ መሃል አመጡት።
​"هذا جزاء من يهرب!"

"ይሄ ለማምለጥ የሚሞክር ሰው ቅጣት ነው!"

እያለ ደላላው በጅራፍ ልጁን ይገርፈው ጀመር።
​ኦርሳም አይኑን ጨፈነ። እዚህ ቦታ ህግ የለም፣ እዚህ ቦታ ርህራሄ የለም ያለው ስራ፣ ስቃይና ሞት ብቻ ነው ያ ያሰበው ስድስት ወር እንደ ስድስት ሺህ ዘመን ረዘመበት።

​ያ የታፈነ ድቅድቅ ጨለማ በጅራፍ ድምፅና በሚያሳቅቅ ጩኸት ተሞላ ኦርሳም አይኑን ጨፍኖ የልጁን ስቃይ ቢሰማውም በውስጡ የሚሰማው ህመም ግን ከጅራፉ በላይ ነበር
"ሰው... እንዴት ለሰው እንዲህ ይጨክናል?" የሚለው ጥያቄ ጭንቅላቱን ሊያፈነዳው ደረሰ ስድስት ወር እንዲህ ባለ ጀሃነም ውስጥ መቆየት ማለት መሞት መሆኑ ገባው።

​ጎህ ሲቀድ ዘበኞቹ በዱላ ድንኳኑን እየመቱ ቀሰቀሷቸው። ኦርሳም ትላንት ከሰል ሲያካፋ በወጡት ፊኛዎች ላይ የከሰሉ አቧራ ገብቶ እጆቹ እንዲያብጡ አድርጓቸዋል  ጣቶቹን ማጠፍ አቅቶታል።


​የወይዘሮ ጀሚላ ቤት አሁን ጭር ብሏል ጎረቤቶች መጥተው "አይዞሽ" ማለቱን ሰልችተውታል ዛሬ ግን የቤት አከራያቸው አቶ በሽር ደጃፍ ላይ ቆመዋል
​"ወይዘሮ ጀሚላ... አውቃለሁ ችግር ላይ ነሽ ግን እኔም የምተዳደረው በዚህ ነው። የሁለት ወር ኪራይ ካልተከፈለ ቤቱን መልቀቅ አለባችሁ" አሏቸው ፊታቸውን አዙረው።

​ወይዘሮ ጀሚላ ልባቸው በሃዘን ተሰበረ " በሽር ... ልጄ ለስራ ሄዶ እኮ ነው... እስኪመለስ ድረስ" ብለው ቢማጸኑም አከራዩ ግን "ልጅሽ የት እንደሄደ ሰምተናል በረሃ የገባ ሰው ደግሞ የሚመለስ ይመስልሻል ?" ብለው በቁስላቸው ላይ እንጨት ሰደዱባቸው። ወይዘሮ ጀሚላ ደጃፉ ላይ ቁጭ ብለው ምርር ብለው አለቀሱ ሀኪያ ግን በክሊኒኩ ውስጥ ሆና ይሄን ሁሉ አታውቅም የምትጠብቀው ወንድሟን ብቻ ነው።


​ኦርሳም ዛሬም እንደ ትላንቱ አካፋውን አንስቷል ፀሐይዋ ልክ 12 ሰዓት ሲሆን ንዳዷን መርጨት ጀመረች በአጠገቡ ያለው ሶማሌያዊ ወጣት በድካም መንቀጥቀጥ ጀምሯል ኦርሳም እጁን እየመመመውም ቢሆን ወደ ልጁ ጠጋ ብሎ አይዞህ በሚል ምልክት ያገዘው ጀመር
​በመሃል ግን አንድ ያላሰበው ነገር ተከሰተ ትላንት ማምለጥ የሞከረውን ልጅ የገረፈው ያ ግዙፍ ሱዳናዊ ወደ ኦርሳም ቀረበ ኦርሳም ለጥቃት የተዘጋጀ ይመስል ደረቱን ነፋ ሱዳናዊው ግን ዛሬ ቁጣ አልታየበትም።
​"انت اثيوبي؟"
(አንተ ኢትዮጵያዊ ነህ? አለው

ኦርሳም አማርኛ እንጂ አረብኛ እንደማይችል ቢታወቅም "ኢትዮጵያ" ብሎ መለሰ።"

​ሱዳናዊው ዝቅ ባለ ድምፅ "እኔም እናቴ የናንተ ዘር ናት ግን እዚህ ቦታ ላይ ማንም አያውቅም ሳይህ ታታሪ ነህ ከሁሉም ትለያለህ " አለውእየተንተባተበ በአማርኛ ኦርሳም በድንጋጤ አየው ። ሱዳናዊው ከኪሱ አንድ ትንሽ ቁራጭ ዳቦ አውጥቶ በከሰል ወደ ተለወጠው የኦርሳም እጅ አቀበለውና "በፍጥነት ብላው" ብሎት ዞር አለ።
​ኦርሳም ያቺን ዳቦ ለሁለት ከፍሎ ግማሹን ለሶማሌያዊው ጓደኛው ሰጠው። ያቺ ዳቦ ለኦርሳም የዛሬው ብርታት ሆነችው።

​.......
.......
............
ከ 100🥰 ቡሃላ .......
#ክፍል_6_ይቀጥላል☆....
❤75👍5😢2
September 8, 2026 1.5K 2 8