ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 289❵ #hadith289 "አቡ ዐብዳላህ ሑዘይፈት ኢብኑ አል-የማን (ረ.ዐ)… — 𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋 — TG.ME

𝐇𝐚𝐟𝐮 𝐢𝐬𝐥𝐚𝐦𝐢𝐜 𝐩𝐨𝐬𝐭™🕋✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 288❵ #hadith288 "አቡ ሁረይራ (ረዐ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ተከታዩን ተናግረዋል። "እሳት አጓጊ በሆኑነገሮች (በስጋዊ ፍላጎቶችና ስሜቶች) ተጋርዳለች። ጀነት ደግሞ አስቸጋሪና ተፈታታኝ በሆኑ ነገሮች ተጋርዳለች።" (ቡኻሪና ሙስሊም) 📋ያለፈው ክፍል👇📋 https://t.me/Hafu_posts/18237 🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ…
ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ

❴Part 289❵ #hadith289


"አቡ ዐብዳላህ ሑዘይፈት ኢብኑ አል-የማን (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፡-

"አንድ ቀን ሌሊት ከነብዩ (ሶ.ዐ.ወ) ጋር (እርሳቸውን ተከትዬ) ሰገድኩ፡፡ የቁርኣን ንባባቸውን ከአል-በቀራህ ምዕራፍ ጀመሩ፡፡ "ሶስት አንቀጾችን ካነበቡ በኋላ ሩኩዕ ያደርጋሉ" የሚል ሃሳብ አደረብኝ። መቶኛውን አንቀጽ አለፉና ንባባቸውን ቀጠሉ፡፡ ምዕራፉን እንዳጠናቀቁ ሩኩዕ እንደሚያደርጉ ገመትኩ። ምዕራፉን አጠናቀቁ፡፡ "አሁን ሩኩዕ ሊያደርጉ ነው" አልኩኝ (በሃሳቤ) ፡፡ አላደረጉም፡፡ የአል -ኒሳዕ ምዕራፍን ማንበብ ጀመሩ፡፡ አጠናቀቁም አል-ዒምራንን ጀመሩ።
እርሷንም አጠናቀቁ፡፡ የሚያነቡት ረጋ በለው ነበር፡፡ ስለአላህ ጥራትና ልዕልና የሚናገር አንቀጽ ሲገጥማቸው "ሱብሓነላህ ( ለአላህ ጥራት ይገባው)" ይላሉ። ጥያቄያዊ አንቀጽ ሲገጥማቸው ይጠይቃሉ። የአላህን ጥበቃ ሲያነሱ አላህን ጥበቃውን ይማጸናሉ፡፡ ሩኩዕ አደረጉና "ሱብሓነ ረቢየል ዐዚም" ይሉ ጀመር፡፡ ሩኩዓቸው የቆሙበትን ያክል የወሰደ ነው፡፡ "ሰሚዐላሁ ሊመን ሃሚዳህ፥ ረበና ለከል ሃምድ" በማለት ከሩኩዕ ተነሱ፡፡ ሩኩዕ ያሉትን የጊዜ ርዝመት ያክል ቆመው ቆዩ፡፡ ከዚያ ሱጁድ ወረዱ፡፡ "ሱብሃነ ረቢየል አዕላ" አሉም፡፡ ሱጁዳቸው የቆሙበትን ያህል ጊዜ የሚመጥን ነበር፡፡"

(ሙስሊም ዘግበውታል)



📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/18280

🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
🥰9❤5👏1
September 2, 2026 2.1K 2 3