✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨
❴Part 281❵ #hadith281
"የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) የኸይበር ዕለት "ይህንን ሰንደቅ አላህንና መልዕክተኛውን በእጀጉ ለሚያፈቅር ሰው እሰጣለሁ፡፡ አላህ በዚህ ሰው እጅ ለድል ያበቃናል" አሉ። ዑመር (ረ.ዐ)፡- "ከዚያን ቀን ውጪ ሹመትን ተመኝቼ አላውቅም፡፡ (የዚህ ታላቅ እድል ባለቤት በመሆን) እጠራ ይሆናል በሚል ተስፋ እንንጠራራ ነበር -(ለመታየት)፡፡ የአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ) ዐሊይን(ረ.ዐ) ጠሩ፡፡ ሰንደቅ አላማውንም አስረከቡት፡፡ "አላህ ለድል እስኪያበቃን ድረስ ወደፊት ቀጥል፡ ወደሗላ አትዙር" አሉትም፡፡" ብለዋል ዐሊይ (ረ.ዐ) ጥቂት ተጓዘናቆመ፡ ወደሗላ አልዞረም፡፡ " የአላህ መልዕክተኛ ሆይ!ሰዎችን የምዋጋቸው ለምን ዓላማ ነው?" ሲል ጠየቀ፡፡ ከአላህ ውጪ ሌላ አምላክ አለመኖሩንና ሙሐመድም የአላህ መልዕክተኛ መሆናቸውን አስኪመሰክሩ ድረስ ተፋለማቸው። ይህንን ካደረጉ ደማቸው፥ ገንዘባቸውም፥ ህጋዊ በሆነ መልኩ ካልሆነ በቀር፥ ካንተ የተጠበቀ ነውሌሎች ተግባሮቻቸውን መተሳሰብ ከአላህ ነው" አሉት፡፡
(ሙስሊም ዘግበውታል)
📋ያለፈው ክፍል👇📋
https://t.me/Hafu_posts/17866
🚫ለወዳጆቻችሁ በመላክ ከአጅሩ ተካፈሉ🚫
13August 23, 2026 2.7K 1