✞ ዐረገች በስብሐት ✞
ዐረገች በስብሐት ዐረገች በእልልታ
በስብሐት በእልልታ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
የጻድቃን እመቤት የሀጥአን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
የማይታበለው እንዲፈጸም ቃሉ
ብታርፍም እመአምላክ ቤዛዊተ ኩሉ
ዐረገች ተነስታ ድንግል የእኛ እናት
እልል በሉላት እልል በሉላት
የጻድቃን እመቤት የሀጥአን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
/አዝ=====
ሰማያት ተደንቀው በአዲሲቷ ሰማይ
ያልቻሉትን ጌታ ወስናው ብትታይ
ሊቀበሏት ወጡ በሐሴት በሙሉ
ንዒ ንዒ እያሉ ንዒ ንዒ እያሉ
የጻድቃን እመቤት የሀጥአን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
/አዝ=====
ዘመኗን በሙሉ ስለ ልጇ አልቅሳ
የመከራ ሰይፍን አሳልፋ ነፍሷ
በቀኙ ልትቆም ንግስት እየተባለች
ይኸው ዐርጋለች ይኸው ዐርጋለች
የጻድቃን እመቤት የሀጥአን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
/አዝ=====
በሐዋርያት አበው ትምህርት የጸናችሁ
የልጇ ምስክር ከዘሯ የቀራችሁ
ከሞት ተነስታለች ቅድስት እናታችሁ
እንኳን ደስ ያላችሁ እንኳን ደስ ያላችሁ
የጻድቃን እመቤት የሀጥአን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
/አዝ=====
ልጅሽ በዳሰሰው በነካው ሰበን
እንደባረክሻቸው ሐዋርያቱን
ማርያም ማርያም ስንል ደጅሽ ላይ ቆመን
እኛንም ባርኪን እኛንም ባርኪን
የጻድቃን እመቤት የሀጥአን ተስፋ
ዐረገች ዐረገች በእልልታ
እንኳን አደረሳችሁ!
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
❖ @Gamel_Media ❖ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞