#Freshman_Course
➡️በ2019 ዓ.ም ዩኒቨርሲቲ የምትገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ( Natural science) ተማሪዎች በመጀመሪያው ሴሚስተር ስለምትወስዷቸው ኮርሶች መረጃ በጥቂቱ 🤗
🕊የመጀመሪያ አመት የመጀመርያው ሴሚስተር ላይ የ ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የምትወስዷቸው ኮርሶች👇
👉 MATHEMATICS (For Natural Science)
👉 GENERAL PHYSICS
👉 GEOGRAPHY
👉 LOGIC & CRITICAL THINKING
👉 COMMUNICATIVE ENGLISH SKILL l
👉 PSYCHOLOGY
👉 PHYSICAL FITNESS
🙌 እስኪ አሁን ደግሞ እያንዳንዱን ኮርሶች እንመልከት።
1⃣ MATHEMATICS
👉 11ኛ እና 12ኛ ክፍል የተማራችሗቸው ናቸው:: የተወሰነ ለውጥ(Modification) ነው ያለው። ስለዚህ ብዙም አትቸገሩበትም አሪፍ ውጤት መስራት ትችላላችሁ👌።
2⃣ General Physics
👉 Revision of grade 11&12🤷
3⃣ Logic and critical thinking
👉ይህ course ለእናንተ አዲስ ነው። ምክንያታዊነት እና ፍልስፍስና የትምህርቱ መሰረት ናቸው።
👉 የConcept ተማሪ ከሆናችሁ እና English ቋንቋ የምትሞክሩ ከሆናችሁ ትሰሩታላችሁ። ይህ ኮርስ በዋናነት የእናንተን የመረዳት ክህሎት ይጠይቃል:: እጅግ በጣም በጣም በጣም ደስ የሚል ኮርስ ነው😊። ነገር ግን ጥልቅ ንባብ እና መረዳት ይጠይቃል፤ ላይ ላዩን ማንበብ የለባችሁም☹️።
👉 ለLogic and Critical Thinking የሚያግዝ እጅግ በጣም ምርጥ አጋዥ መፅሀፎች አሉ።
▪️ Concise introduction to logic
▪️ Freshman Logic
🔒 Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ በጣም አሪፍ አድርጎ ያስረዳል። በጣም አሪፍ አሪፍ የሚባሉ እና ከበድ ያሉ ጥያቄዎችም አሉት። የዚህን መፅሀፍ ጥያቄዎቹን ገብቷችሁ በአግባቡ ከሰራችሁ ፡ በእርግጠኝነት ግቢ ላይ የሚወጣውን ፈተና ትሰሩታላችሁ 😉
✍️ Freshman logic የሚለው መፅሀፍ ደግሞ የlogic and critical thinking ትምህርትን በቀላሉ እንድትረዱት ያደርጋል ምክንያቱም በ አማርኛ እየተረጎመ ስለሚያስረዳ፤ የትምህርቱን ፅንሰ ሀሳብ (Concept) በቀላሉ ለመረዳት Freshman Logic የሚለው መፅሀፍ በጣም ምርጥ ነው። በዛ ላይ እጅግ በጣም ደስ ደስ የሚሉ የConcept ጥያቄዎችም አሉት😍። ስለዚህ እኛ የምንመክራችሁ
1ኛ. መምህሩ የሚሰጣችሁን ኖት PDF ማንበብ ፡መምህሩ ሲያስተምር በ ደንብ መከታተል። ጥሩ አድርጎ የማያስተምር መምህር ሊያጋጥማችሁ ስለሚችል ነባር ተማሪዎችን ጠይቆ መረዳት።
2ኛ. እኛ የምንሰጠውን ቱቶሪያል በሚገባ ተከታተሉ ጥያቄም አብራችሁ ስሩ፤ እውነት ለመናገር ጠንክራችሁ ከሰራችሁ ጥሩ ዉጤት ታመጣላችሁ 💯
3ኛ. Freshman logic የሚለውን መፅሀፍ ማንበብ ምክንያቱም መፅሀፉ ላይ የቀረቡት ኖቶችን በቀላሉ ስለምትረዷቸው።
4ኛ. Concise introduction to logic የሚለው መፅሀፍ ላይ ሂዳችሁ ጥያቄ መፍለጥ የሚገራርሙ ጥያቄዎች አሉት። ከዛ A+ ታመጡና መቀወጥ🙂
4⃣ Communicative English skill-1
👉 ይህ ኮርስ ላወቀበት ተማሪ የሚሰራ ኮርስ ነው፡ ግቢ ላይ ውጤታችሁን ከሚያነሱ ኮርሶች መካከል ነው። በውስጡ ምን ምን ይዟል መሰላችሁ🤔
👉 Speaking skill (ራሳችሁን በ እንግሊዝኛ ማስተዋወቅ ፡ ከዛ መምህሩ የሆነ ርዕስ ይሰጣችሁ እና ስለዛ ነገር በእንግሊዝኛ presentation ማቅረብ (የሆነ ማርክ%)
👉 Reading skill ( አንድ passage ይሰጣችሗል ፡ በዛ መሰረት ጥያቄ ይሰጣችሗል( የሆነ ማርክ%)
👉 Writing skill ( letter , descriptive ,narrative, argumentative , expository ከነዚህ ባንዱ ትፅፋላችሁ( ከዛ የሆነ ማርክ)
👉 Grammar (Tense , Active and passive voice , conditional sentence, reported speech ... እነዚህ ነው የምትማሩት ፡ ደግሞ ቀላል ናቸው 🥰
5⃣ Geography
👉 ለGeography ም አዲስ አይደላችሁም።
6⃣ Psychology
👉 ይህ ኮርስ በብዙ መልኩ አድስ ሊሆንባችሁ ይችላል ግን biology ማንበብ ስለለመዳችሁ አትቸገሩም። theory ነው ከእናንተ የሚጠበቀዉ ማንበብ ብቻ ኘው😉
7⃣ Physical fitness
👉 ሜዳ ወጥታችሁ ሱምሶማ መስራት መሮጥ ነው፤ ስለዚህ የስፖርት ትጥቅ ያስፈልጋችሗል ፡ እንዳትረሱ😂። ይህ ኮርስ ውጤት የለውም ማለቴ ውጤት አይሰራለትም ዝም ብላችሁ ሜዳ ወታችሁ ትሰራላችሁ እንጅ Grade ( A , A- , B+ ,B , C ....) የለውም። pass or fail ነው የምትባሉት። Attendance ወይም በዚህ ኮርስ ክፍለ ጊዜ ካልቀራችሁ pass ትሆናላችሁ።
👉 ነገር ግን አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች የመጀመሪያው ሴሚስተር ላይ በ Logic and critical thinking ቦታ emerging technology የሚያስተምሩ አሉ ። ከዛ second semester ላይ ደግሞ logic and critical thinking ያስተምራሉ። ብቻ ምንም ለውጥ የለውም ፡ እንድታውቁት ያክል ነው😇
8⃣Emerging technology
👉 ይህ ኮርስ ለእናንተ አዲስ አይደለም። ከ9 - 12 የተማራችሗቸው የ Ict ትምህርቶችን ያካትታል ( Ms word , Ms PowerPoint, Ms excel , database ..... ወዘተ) ነገር ግን በብዙ ግቢዎች በሁለተኛው ሴሚስተር ይሰጣል::
💻ለማስታወስ ያክል
✅First semester ( 50%)
✅Coc exam ( 30%)
✅Entrance exam( 20%)
(Excluding AAU)
JOIN: @FRESmw