መዝሙር 73 (የአሳፍ መዝሙር።) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እንዴት ቸር ነው። ² እኔ ግን እግሮቼ ሊሰናከሉ፥ አረማመዴም ሊወድቅ ትንሽ ቀረ። ³ የኃጢአተኞችን ሰላም አይቼ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና። ⁴ ለሞታቸው መጣጣር የለውምና፤ ኃይላቸውም ጠንካራ ነውና። ⁵ እንደ ሰው በድካም አልሆኑም፥ ከሰው ጋርም አልተገረፉም። ⁶ ስለዚህ ትዕቢት ያዛቸው፤ ኃጢአትንና በደልን ተጐናጸፉአት። ⁷ ዓይናቸው ስብ ስለ ሆነ ወጣ፤ ልባቸውም ከምኞታቸው ይልቅ አገኘ። ⁸ አስበው ክፉ ነገርን ተናገሩ፤ ከፍ ከፍ ብለውም በዓመፃ ተናገሩ። ⁹ አፋቸውን በሰማይ አኖሩ፥ አንደበታቸውም በምድር ውስጥ ተመላለሰ። ¹⁰ ስለዚህ ሕዝቤ ወደዚህ ይመለሳሉ፤ ፍጹም ጊዜም በላያቸው ይገኛል፤ ¹¹ እግዚአብሔር እንዴት ያውቃል? በልዑልስ ዘንድ በውኑ እውቀት አለ? ይላሉ። ¹² እነሆ፥ እነዚህ ኃጢአተኞች ይደሰታሉ፥ ሁልጊዜም ባለጠግነታቸውን ያበዛሉ። ¹³ እንዲህም አልሁ፦ በውኑ ልቤን በከንቱ አጸደቅሁ፥ እጆቼንም በንጽሕና በከንቱ አጠብሁ። ¹⁴ ሁልጊዜም የተገረፍሁ ሆንሁ፥ መሰደቤም በማለዳ ነው። ¹⁵ እንደዚህ ብዬ ብናገር ኖሮ፥ እነሆ፥ የልጆችህን ትውልድ በበደልሁ ነበር። ¹⁶ አውቅም ዘንድ አሰብሁ፥ ይህ ግን በፊቴ ችግር ነበረ። ¹⁷ ወደ እግዚአብሔር መቅደስ እስክገባ ድረስ፥ ፍጻሜአቸውንም እስካስተውል ድረስ። ¹⁸ በድጥ ስፍራ አስቀመጥኻቸው፥ ወደ ጥፋትም ጣልኻቸው። ¹⁹ እንዴት ለጥፋት ሆኑ! በድንገት አለቁ ስለ ኃጢአታቸውም ጠፉ። ²⁰ ከሕልም እንደሚነቃ፥ አቤቱ፥ ስትነቃ ምልክታቸውን ታስነውራለህ። ²¹ ልቤ ነድዶአልና፥ ኵላሊቴም ቀልጦአልና፤ ²² እኔ የተናቅሁ ነኝ አላውቅሁምም፥ በአንተ ዘንድም እንደ እንስሳ ሆንሁ። ²³ እኔ ግን ዘወትር ከአንተ ጋር ነኝ፥ ቀኝ እጄንም ያዝኸኝ። ²⁴ በአንተ ምክር መራኸኝ፤ ከክብር ጋር ተቀበልኸኝ። ²⁵ በሰማይ ያለኝ ምንድር ነው? በምድርስ ውስጥ ከአንተ ዘንድ ምን እሻለሁ? ²⁶ የልቤ አምላክ ሆይ፥ ልቤና ሥጋዬ አለቀ፤ እግዚአብሔር ግን ለዘላለም እድል ፈንታዬ ነው። ²⁷ እነሆ፥ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉና፤ ከአንተ ርቀው የሚያመነዝሩትንም ሁሉ አጠፋኻቸው። ²⁸ ለእኔ ግን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሻለኛል፤ መታመኛዬም እግዚአብሔር ነው በጽዮን ልጅ በሮች ምስጋናህን ሁሉ እናገር ዘንድ። Join us 📚@Holy_scriptures📚 📚@Holy_scriptures📚 ይ🀄️ላ🀄️ሉን
መዝሙር 73 (የአሳፍ መዝሙር።) ¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯ ¹ ልባቸው ለቀና ለእስራኤል እግዚአብሔር እንዴት ቸር ነው።… — ክርስትና (kiristiyanummaa) — TG.ME
April 10, 2025 1.2K 1