🇪🇹🇪🇷 የማለዳው ቃል 🇪🇹🇪🇷
"¹⁵ የዋህ ቃልን ሁሉ ያምናል፤ ብልህ ግን አካሄዱን ይመለከታል።" ምሳሌ 14፥15 1954 እትም
"ሞኝ ሰው የሚነግሩትን ሁሉ አምኖ ይቀበላል፤ ብልኆች ግን እርምጃቸውን በጥንቃቄ ይመረምራሉ።" ምሳሌ 14፥15 2005 መደበኛ ትርጉም
🔥 ሻሎም ሻሎም እንደምን አደራችሁ ቅዱሳን ዛሬ የምንካፈለውን ቃል በተሻለ ሁኔታ እንድትረዱት ከመፅሃፍ ቅዱሳችን በመደበኛው እና በትርጉም ያለውን አስቀምጬላችዋለው
🔥 እንደምታውቁት የምሳሌ መፅሃፍ ፀሃፊ ሰለሞን ነው ሰለሞን በዚህ ክፍል ሞኝ አትሁኑ ነው የሚለው ሞኝጨሰው የተሰጠውን ሁሉ ይቀበላል ይላል ይጠቅመኛል አይጠቅመኝም የሚለውን ነገር አያይም ሁሉንም ነው የሚቀበለው
🔥 ብልህ ሰው ግን እርምጃውን ይመረምራል ያስተውላል ይጠቅማል አይጠቅምም በህይወቴ ላይ ምን ለውጥ ያመጣል በመንፈሳዊ ህይወቴ ላይ ምን ተፅኖ ይፈጥራል የሚለውን ሁሉ ይመረምራል የተሰጠውን ሁሉ አይቀበልም ከጌታ ነው ወይ የሚለውንም ያጣራል
🔥 ቅዱሳን ትላንት እንዳልኳችሁ በሰውኛ አቆጣጠር አሮጌውን አመት ዘግተን አዲሱን የምንቀበልበት ነው በዚህ ጊዜ ላይ እራሳችንን በዚህ ቃል እንፈትሽ ደክመን ሞኞች ሆነን ከሆነ በሚመጣው ጊዜ ብልሆች እንድንሆን እንፀልይ እራሳችንንም ለመለወጥ እንነሳ ተባረኩ እወዳችኋለሁ
" ከኢየሱስ ጋር መሆን ደስ ይላል "
👉 ውድ 🇪🇹 ኢትዮጵያውያን 🇪🇹 እና 🇪🇷 ኤርትራውያን 🇪🇷 ወንድሞቼ እህቶቼ ይህ እናንተን በእግዚአብሔር ቃል ለማነፅ አብሮ ለመፀለይ የተከፈተ የቴሌግራም ቻናል ስለሆነ ጆይን ያድርጉ ብሩካን ናችሁ ❤❤❤
👇👇👇👇👇👇
🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢🟢
🟡 @elroichrist 🟡
🟡 @elroichrist 🟡
🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴🔴
" መልካም ቀን"