ወራቤ[ ደርሶች እና ፈዋኢዶች ] (@fewaidworabe) — Telegram — TG.MEወራቤ[ ደርሶች እና ፈዋኢዶች ]
@fewaidworabe · 2.8K subscribers
Share channel “ወራቤ[ ደርሶች እና ፈዋኢዶች ]”
The short link opens the channel straight in the Telegram app — not in a browser tab.
tg.me/go/fewaidworabe
Is this your channel? Add @tgme as admin — and see how many people click your links. Get the stats →
Channel created April 2, 2017per Telegram
We have been tracking it since August 14, 2026
In all that time the channel has changed neither its name, nor its @username, nor its avatar.
We show only what we have seen ourselves.
Who advertises in @fewaidworabe

No ad posts detected
The channel has not run third-party ads in the last 90 days.
Ad analytics →Reviews
0Log in to leave a reviewLog in No reviews yet
Be the first to share your experience with this account.
Write a reviewክፍል 1፡ ከቁርኣንና ከሐዲሥ አንጻር፦
.ዲናችን ሙሉ ነው፦
አላህ በቁርኣኑ «ዛሬ ኃይማኖታችሁን ለእናንተ ሞላሁላችሁ፤ ጸጋዬንም በላያችሁ ላይ ፈጸምኩ» (አል-ማኢዳህ፡ 3) ብሏል። መውሊድ መልካም ተግባር ቢሆን ኖሮ ያኔውኑ በዲናችን ውስጥ በተካተተ ነበር።
. ነቢዩ ﷺ «በዚህ በዲናችን ውስጥ ከርሱ ያልሆነን አዲስ ነገር የፈጠረ ሥራው ተመላሽ (ውድቅ) ነው» ብለዋል (ቡኻሪና ሙስሊም)።
. ነቢዩ ﷺ በየሳምንቱ ኹጥባቸው ላይ «አደራችሁን በዲን ላይ አዳዲስ ፈጠራዎችን! ማንኛውም ፈጠራ ቢድዐ ነው፤ ማንኛውም ቢድዐ ደግሞ ጥመት ነው» እያሉ ያስጠነቅቁ ነበር።
.የፍቅር መለኪያ መከተል ብቻ ነው፡ አላህ የፍቅሩን ማረጋገጫ ያደረገው መከተልን (ኢቲባዕን) እንጂ አዲስ አከባበር መፍጠርን አይደለም፦ «አላህን የምትወዱ እንደሆናችሁ ተከተሉኝ፤ አላህ ይወዳችኋልና» (አሊ-ዒምራን፡ 31)።
.በዲን ውስጥ ድንበር ማለፍ ተከልክሏል። ነቢዩ ﷺ «ክርስቲያኖች የመርየምን ልጅ (ዒሳን) ድንበር አልፈው እንዳወደሱት እኔን ድንበር አልፋችሁ እንዳታወድሱኝ» ብለው አስጠንቅቀዋል (ቡኻሪ)።
.ነቢዩ ﷺ በ23 ዓመታት የነቢይነት ዘመናቸው አንድም ቀን የልደት ቀናቸውን በዓል አድርገው አክብረው ወይም እንዲከበር አዘው አያውቁም።
.የልደት ቀናቸውን ያሳለፉት በጾም ነበር፡ ነቢዩ ﷺ ስለ ሰኞ ቀን ጾም ተጠይቀው «… የተወለድኩበት ቀን ነው» ብለዋል (ሙስሊም)። ታዲያ ፍቅራቸው የሚገለጸው ሰኞን በመጾም ነው ወይስ በዓመት አንዴ በጭፈራና በድግስ?
. በዲን ህግ የማውጣት ስልጣን የአላህ ብቻ ነው፡ «ለእነርሱ አላህ ያልፈቀደውን ከኃይማኖት የደነገጉላቸው ተጋሪዎች አሉዋቸውን?» (አሽ-ሹራ፡ 21)።
.በኢስላም ማንኛውም የአምልኮ ተግባር (ዒባዳህ) ትክክለኛ የቁርኣን ወይም የሐዲሥ መረጃ ካልመጣበት በስተቀር ማድረግ አይፈቀድም። ለመውሊድ ደግሞ አንድም መረጃ የለም።
የኸሊፋዎችን መንገድ ያዙ ተብለናል። ነቢዩ (ኘለﷺ) «የእኔን ሱና እና ከእኔ በኋላ ያሉትን ቅን ኸሊፋዎች ሱንና አጥብቃችሁ ያዙ» ብለዋል፤ እነርሱ ደግሞ መውሊድን አላከበሩም።
ክፍል 2፡ ከሶሐቦች፣ ከታቢዒዮችና ከኢማሞች አንጻር (11–20)፦
አቡበክር ሲዲቅ ይህን በዓል አላከበሩትም። ከነቢያት ቀጥሎ በምድር ላይ ከማንም በላይ ነቢዩን ﷺ የሚወዱት አቡበክር መውሊድን አላከበሩም።
ዑመር ኢብኑል ኸጣብ አላከበሩትም፡ ዲንን ከፍ ያደረጉት ዑመር ለነቢዩ ልደት በዓል አላቋቋሙም።
ዑሥማን ኢብኑ ዐፋን አላከበሩትም። ሁለት የነቢዩን ልጆች ያገቡት ዑሥማን ይህን አላደረጉም።
. ዐሊይ ኢብኑ አቢ ጧሊብ አላከበሩትም፡ የነቢዩ የቅርብ ቤተሰብ (አህለል በይት) መሪ የሆኑት ዐሊይም አላከበሩትም።
. ሐሰንና ሑሰይን (ረ.ዐ) አላከበሩትም፡ የነቢዩ የልጅ ልጆችና የጀነት ወጣቶች አለቆች የሆኑት እነርሱ እንኳን የውድ አያታቸውን ልደት አላከበሩም።
. የሙእሚኖች እናቶች (የነቢዩ ሚስቶች) አላከበሩትም፡ ከማንም በላይ የነቢዩን የቤት ውስጥ ህይወት የሚያውቁት እናቶቻችን (ዐኢሻ፣ ኸዲጃ...) አላከበሩትም።
. ሶሐቦች ከእኛ በላይ ነቢዩን ይወዱ ነበር፡ እኛ ሶሐቦች ለነቢዩ ከነበራቸው ፍቅር አንድ ቅንጣት እንኳን አይኖረንም። እነርሱ ያልሰሩትን በጎ ስራ እኛ አገኘን ማለት ራስን ማታለል ነው።
. ምርጦቹ ሦስት ክፍለ ዘመናት (ኸይሩል ቁሩን)፡ ነቢዩ (ﷺ) «ከሁሉ በላጩ ትውልድ የእኔ ትውልድ ነው፤ ከዚያም የሚከተሏቸው...» ያሉላቸው ሦስቱ ትውልዶች መውሊድ የሚባል ነገር አያውቁም ነበር።
. አራቱ ታላላቅ መዝሃብ ኢማሞች አላከበሩትም፡ ኢማም አቡ ሐኒፋ፣ ኢማም ማሊክ፣ ኢማም ሻፊዒይ እና ኢማም አሕመድ መውሊድን አላከበሩም፤ በኪታቦቻቸውም አላዘዙም።
ኢማም ማሊክ «በኢስላም ውስጥ ነቢዩ ﷺ ያላደረጉትን አዲስ ነገር 'ጥሩ ነው' ብሎ የፈጠረ ሰው፣ ሙሐመድ ﷺ መልእክቱን አጓድለዋል (ከድተዋል) ብሎ እንደመሰከረ ይቆጠራል» ብለዋል።
ክፍል 3፡ ከሎጂክ አንጻር (21–30)
. ዒባዳ ነው ወይስ ባህል? መውሊድ አጅር የሚያስገኝ ዒባዳ ነው ካልክ መረጃ የለህም፤ ዒባዳ ካልሆነ ደግሞ ለምን አጅር ፍለጋ ትደክማለህ?
. ቀኑ የልደት ነው ወይስ የሞት? በታሪክ ተመራማሪዎች ዘንድ ነቢዩ (ﷺ) የተወለዱበት ቀን (ረቢዐል አወል 9፣ 12 ወይስ ሌላ?) አከራካሪ ነው። የሞቱበት ቀን ግን በእርግጠኝነት ረቢዐል አወል 12 ነው። ታዲያ በሞቱበት ቀን እንዴት ደስታ ይደረጋል?
. ፍቅር የ365 ቀናት እንጂ የአንድ ቀን አይደለም፡ ነቢዩን ማፍቀር በየሰከንዱ፣ በየቀኑ በሱናቸው በመመራት የሚገለጽ እንጂ በዓመት አንድ ቀን ጣፋጭ በመብላትና በመጨፈር የሚገለጽ አይደለም።
. ፍቅርን በዘፈቀደ መግለጽ አይቻልም፡ አንድ ሰው «ነቢዩን ስለምወድ የሱብሒን ሶላት 3 ረከዓ ላድርገው» ቢል ስሜቱ ጥሩ ቢሆንም ስራው ግን ውድቅ ነው። መውሊድም እንዲሁ ነው።
ነቢዩ ﷺ እኛን ከማንም በላይ ያውቁናል፤ የልደታቸው ቀን ማክበር መልካም ቢሆን ኖሮ አንድም ቀን እንኳን እንዲህ አድርጉ ብለው ባስተማሩን ነበር።
አላህ ለሙስሊሞች ሁለት ዓመታዊ በዓላትን (ዒደል ፊጥር እና ዒደል አድሓ) እንዲሁም አንድ ሳምንታዊ (ጁምዓን) ብቻ ሰጥቷል። አራተኛ በዓል መጨመር የሸሪዓን ድንበር መጣስ ነው።
. የነቢዩን ፈለግ መናቅ ይመስላል፡ «እነርሱ ያላደረጉትን እኔ አደርጋለሁ» ማለት በተዘዋዋሪ «እነርሱ ያላወቁትን መልካም ነገር እኔ አውቄያለሁ» የማለት ያህል ትዕቢት ነው።
. የስነ-ልቦና ማታለያ፡ መውሊድ የሚያከብሩ ሰዎች «ነቢዩን አፈቀርን፣ ግዴታችንን ተወጣን» የሚል የውሸት መንፈሳዊ እርካታ ስለሚሰጣቸው እውነተኛውን የሱና ህይወት ቸል እንዲሉ ያደርጋቸዋል።
3️⃣9️⃣. ቅድሚያ የሚሰጠው ተዛብቷል፡ ሱናቸውን በትክክል ከመተግበር ይልቅ በዓመት አንዴ በሚደረግ ስነ-ስርዓት ላይ ትኩረት ማድረግ የቅድሚያ ቅደም-ተከተል መዛባት ነው።
3️⃣0️⃣. የሌሎች ሃይማኖቶች ቅጅ ነው፡ ልደትን ማክበር የነቢያት መንገድ ሳይሆን የሮማውያንና የፋርሶች አረማዊ ባህል ነው።

ክፍል 4፡ ከታሪክ ምንጭ እና ከመጤነት አንጻር (31–40)
3️⃣1️⃣. መቼ ተጀመረ? መውሊድ የተጀመረው ነቢዩ ﷺ በሞቱ በ4ኛው ክፍለ ዘመን (ከ300 ዓመታት በኋላ) ነው።
3️⃣3️⃣. ማን ጀመረው? የጀመሩት አህለ-ሱንናዎች ሳይሆኑ፣ በኢስላም ታሪክ እጅግ የተወገዙት እና አፈንጋጮቹ ፋጢሚዮች (የኡበይዲያ መንግስት) ናቸው።
3️⃣3️⃣. ፋጢሚዮች ምን አይነት ሰዎች ነበሩ? የነቢዩን ሶሐቦች የሚረግሙ፣ የራሳቸውን ንጉሶች ልክ እንደ አምላክ የሚያዩ ከሃዲዎች ነበሩ። ታዲያ የነርሱን ፈሊጥ እንዴት እንከተላለን?
3️⃣4️⃣. የክርስቲያኖች አምሳያ (ተሸቡህ)፡ ፋጢሚዮች መውሊድን የፈጠሩት ክርስቲያኖች የኢየሱስን (ዒሳን) ልደት (ገና/Christmas) ሲያከብሩ አይተው እነሱን ለመምሰል ነው።
3️⃣5️⃣. ነቢዩ (ﷺ) ከካፊሮች መመሳሰልን ከልክለዋል፡ «የአንድን ሕዝብ ወግና ልማድ የተከተለ እርሱ ከእነርሱው ነው» ብለዋል (አቡ ዳዉድ)።
3️⃣6️⃣. የሌሎች መውሊዶች መፈጠር፡ የነቢዩ መውሊድ ሲፈቀድ፣ ቀጥሎ የሸይኾች፣ የደብተራዎችና የቃሊቾች መውሊድ ተፈጠረ፤ ሽርክም በሰፊው ተስፋፋ።
3️⃣7️⃣ በአራቱ የሐዲሥ እና የፊቅህ መጻሕፍት ውስጥ «ኪታቡል መውሊድ» (የመውሊድ ምዕራፍ) የሚባል አንድም ነገር የለም።
3️⃣8️⃣. መከፋፈልን ፈጠረ፡ መውሊድ በሙስሊሙ ማህበረሰብ መካከል የልዩነት እና የጭቅጭቅ በር ከፈተ እንጂ አንድነትን አላመጣም።
3️⃣9️⃣. የቢድዐ ተፈጥሮ፡ አንድ ቢድዐ በህዝብ ዘንድ በነገሰ ቁጥር፣ በዚያው ልክ አንድ የነቢዩ ሱንና ይሞታል (ይረሳል)።
4️⃣0️⃣. የቀደምት ዑለማዎች ማውገዝ፡ እንደ ኢብኑ ተይሚያህ፣ ኢብኑል ቀይም፣ ኢማም አል-ሻጢቢ እና ሌሎችም ታላላቅ የኡማው ሊቃውንት መውሊድ ፈጠራ መሆኑን በመረጃ አረጋግጠዋል።

ክፍል 5፡ በውስጡ ካሉ አደጋዎችና ተጨባጭ ሁኔታዎች አንጻር (41–50)
4️⃣1️⃣. የሽርክ ስንኞች መኖር፡ በመውሊድ ላይ በሚቀሩ መንዙማዎችና ጽሑፎች (እንደ ቡርዳህ) ውስጥ ነቢዩን ከአላህ እኩል የሚያደርጉ፣ የሩቅ አዋቂ እና ሀጃ አውጪ የሚያደርጉ ግልጽ የሽርክ ቃላት ይገኛሉ።
4️⃣3️⃣. የወንዶችና የሴቶች ቅልቅል (ኢኽቲላጥ)፡ በአብዛኞቹ የመውሊድ ስፍራዎች ወንዶችና ሴቶች ተቀላቅለው ይጨፍራሉ፤ ይህም በሸሪዓ ክልክል ነው።
4️⃣3️⃣. የከበሮና የሙዚቃ መሳሪያዎች፡ መስጂዶችና አደባባዮች ለዝክር ሳይሆን ለከበሮ ድለቃና ለጭፈራ መዋላቸው የአምልኮን ክብር ያዋርዳል።
4️⃣4️⃣. የንብረት ብክነት፡ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለጣፋጭ፣ ለጫት እና ለድግስ ሲባክን፣ በርካታ የተራቡና የተቸገሩ ሙስሊሞች ግን የሚበሉት አጥተው ይማቅቃሉ።
4️⃣5️⃣. ሶላት መተው፡ ብዙ የመውሊድ ታዳሚዎች ሌሊቱን ሲጨፍሩ አድረው የሱብሂን ፈርድ ሶላት ያመልጣቸዋል።
4️⃣6️⃣. ጫት እና አደንዛዥ እጾች፡ በአንዳንድ አካባቢዎች መውሊድ ያለ ጫትና ጭስ አይታሰብም፤ ይህም ራስን መበከል ነው።
4️⃣7️⃣. የሐውድ (የወንዙ) አደጋ፡ በቂያማ ቀን ነቢዩ (ﷺ) ከሐውዳቸው ውሃ ሊያጠጡን ሲሉ መላእክት አንዳንድ ሰዎችን ያባርሯቸዋል። ነቢዩም «እነሱ እኮ ተከታዮቼ ናቸው» ሲሉ መላእክቱ «ከአንተ በኋላ በዲንህ ላይ ምን እንደፈጠሩ አታውቅም» ይሏቸዋል (ቡኻሪ)። በቢድዐ ምክንያት ከነቢዩ እጅ መጠጣት እንዳንከለከል አንፈራምን?
4️⃣8️⃣. «ሰዎችን እንመግባለን» የሚለው ሰበብ፡ ምስኪኖችን መመገብ ታላቅ ዒባዳ ነው፤ ነገር ግን ይህ በማንኛውም ቀን በሱንና መንገድ መደረግ ያለበት እንጂ ካልተደነገገ በዓል ጋር ሊያያዝ አይገባም።
4️⃣9️⃣. አላህ ፊት ስንቆም ምን እንመልሳለን? ነገ አላህ ፊት ቀርበህ «ይህን የመውሊድ በዓል እንድታከብር ከቁርኣንና ከነቢዬ ምን ማስረጃ አገኘህ❓» ተብለህ ስትጠየቅ የምትሰጠው መልስ የለህም!
5️⃣0️⃣. እውነተኛው ፍቅር የትኛው ነው? ነቢዩን

በእውነት የሚወድ ሰው እርሳቸው ያዘዙትን ይሰራል፣ የከለከሉትን ይተዋል፣ ሱንናቸውን ያስፋፋል፤ ከፈጠራ (ቢድዐ) ሁሉ ራሱን ያርቃል።
ውድ ወንድሜና እህቴ ሆይ!
ልብህን ጠይቅ፦ ነቢዩ ሙሐመድ (ﷺ) ዛሬ በአይናችን ፊት ቢገኙ ኖሮ፣ እሳቸውም ሆኑ ምርጥ ባልደረቦቻቸው ፈጽመው የማያውቁትን ይህን በዓል እንድናከብር ይፈቅዱልን ነበር? ወይስ «ይህ ፈጠራ ነው ተዉት!» ብለው ይቆጡን ነበር?
መልሱ ግልጽ ነው። እውነተኛ ፍቅር መከተል እንጂ መፍጠር አይደለም!
ስለዚህ ዛሬውኑ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ወስነህ/ሽ የመውሊድ እቅድህን ሰርዝ፤ ይልቁንም ያንን ቀን ነቢዩ ባዘዙት መሠረት በጾም፣ ቁርኣን በማንበብ፣ ሱናቸውን በማጥናት እና በእርሳቸው ላይ ሶለዋት በማውረድ እውነተኛውን የፍቅር መንገድ ምረጥ!
አላህ እውነተኛውን የነቢዩን ﷺ ፈለግ የምንከተል ያድርገን።
||
t.me/MuradTadesse