በሶማሊያ ሰላም ማስከበር የሴክተር 3 መሃንዲስ ክፍል ግዳጁን በላቀ ብቃት እየፈፀመ መሆኑ ተገለፀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 14 ቀን 2019 ዓ.ም
የመሃንዲስ ክፍሉ የሠፈረበት አካባቢ ለጎርፍ አደጋ ተጋላጭ በመሆኑ በየጊዜው ጎርፍ የመከላከል ፈንጅዎችን የማፅዳትና ምሽጎችን የማጠናከር ስራን እየሰራ ይገኛል፡፡
የሴክተር ሶስት መሀንዲስ ክፍል ሃላፊ ሌተናል ኮሎኔል መስፍን አያሌው የመሀንዲስ ክፍሉ ከተሰጡት ሃላፊነቶች መካከል ሰራዊቱንና ለሰላም ማስከበር የተሰማራበትን የማህበረሰብ ክፍል ከሰው ሰራሽና ከተፈጥሮ አደጋ መጠበቅ በዋናነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የመሀንዲስ አባላቱ በተጨማሪ በወሰዱት የተቀነባበረ ፈንጂ የማምከን ስልጠና መሰረት በተለያዩ የግዳጅ ቀጠናዎች በበርደሬ፣ ገብረሃሬ፣ ቀንሰሃደሬ በመዘዋወር ፈንጅ የማፅዳትና የአልሸባብን ሴራ የማክሸፍ ሥራ እያከናወኑ መሆናቸውን ገልፀዋል።
አልሸባብ በተለያዬ ጊዜ በስውር ክብደት ያላቸው የተቀነባበሩ ፈንጂዎችን አጥምዶ የነበረ ቢሆንም በአካባቢው ማህበረሰብ ጥቆማና ባልተቋረጠ የመሃንዲስ ክፍሉ ፍተሻ በሰውና በንብረት ላይ አደጋ ሳያደርስ ማምከን መቻሉን ሌተናል ኮሎኔል መስፍን አያሌው ተናግረዋል።
ዘጋቢ መዝገቡ ያረጋል
ፎቶ ግራፍ ሙላቱ በየነ
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
27
15
1September 24, 2026 6K 1