ኮሩ ያሰለጠናቸውን የጤና ሙያተኞች አስመረቀ።
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት መስከረም 25 ቀን 2019 ዓ.ም
የሰሜን ምስራቅ ዕዝ አንድ ኮር ለወራት ያሰለጠናቸውን የመጀመሪያ ደረጃ የጤና ባለሙያዎችን አስመርቋል።
ወታደራዊ አመራሮች እና የሃራ ከተማ ሲቪል አመራሮች በተገኙበት በተካሄደው የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ ስልጠናው የኮሩን የውጊያ ዝግጁነት የማረጋገጥ አካል መሆኑ ተገልጿል።
በዕለቱ የሐራ ከተማ አስተዳደር ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፋንታሁን በለጠ የሠራዊቱን ሁለንተናዊ አቅም የማሳደግ ተግባራት ከሀገር እና ከህዝብ ሰላም ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ጉዳይ በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል ብለዋል።
ሠራዊታችን በሚያከናውናቸው ህግ የማስከበር ዘመቻዎች የአካባቢው ማህበረሰብና አስተዳደር እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከሠራዊቱ ጎን ሆኖ የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ እያበረከተ እንደሚገኝ ጠቅሰው ይህ ተግባር እስከ መጨረሻው ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ተናግረዋል።
ሌተናል ኮሎኔል ገዙ ሚልኪ በበኩላቸው በሠራዊቱ ግዳጅ ውስጥ የጤና ሙያተኞች አስፈላጊነት የላቀ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ወሳኝ የግዳጅ ወቅት ስልጠናው መጠናቀቁ ለኮሩ ተልዕኮ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረክታል ብለዋል። ዘገባው የኮሩ የሠራዊት ስነ-ልቦና ግንባታ ነው
የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/
https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2
https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0
https://www.facebook.com/fdredefense.official
30
16
2October 5, 2026 6.8K 1