23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የባህል ትውውቅ እና ስፖርታዊ ውድድር፦ የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት… — FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት — TG.ME

23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ የባህል ትውውቅ እና ስፖርታዊ ውድድር፦

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ነሃሴ 24 ቀን 2018 ዓ.ም

ሻለቃው በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልዕኮ (unmiss ) ጥላ ስር  በደቡብ ሱዳን ምዕራብ ኢኳቶሪያ ግዛት ከተሰማሩ የተለያዩ ሰላም አስከባሪ ሀገራት ጋር የመረብ ኳስ ውድድር እና የኢትዮጵያን የባህል ምግብ ትውውቅ አድርጓል።

የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ሻለቃ አበበ አንሽሶ ፤ የባህል ትውውቅና ስፖርታዊ ውድድሩ በደቡብ ሱዳን የተሰማሩ ሀገራት ሰላም አስከባሪ አባላት ግንኙነትን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል።

በወንድማማችነት እና በመተባበር ላይ የተመሰረተ ግንኙነት የሰላም ማስከበር ስራውን የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደረገው የገለፁት ሃላፊው ፤ ከሀገራቱ ጋር የሚደረገው ግንኙነት በቀጣይነትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አስረድተዋል።

የዝግጅቱ ተሳታፊዎች ኢትዮጵያ በተባበሩት መንግስታት እና በአፍሪካ ህብረት የሰላም ማስከበር  ተልዕኮዎች ረጅም እና የሚያኮራ ታሪክ ያላት ታላቅ ሀገር መሆኗን ገልፀው ፤ የኢትዮጵያ ወታደር ለደቡብ ሱዳን ህዝብ ሰላም እየከፈለ ካለው መስዋዕትነት ባለፈ ለወገኑ ያለው ፍቅር እና ወታደራዊ ዲስፒሊን የሚደነቅ ነው ብለዋል ።

በዝግጅቱ የኢትዮጵያ ባህላዊ ምግቦች ፣ የብሄር ብሄረሰብ አልባሳት እና ውዝዋዜዎች የቀረቡ ሲሆን በመረብ ኳስ ውድድር የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ ተወዳዳሪዎችን በማሸነፍ ዋንጫ አንስቷል።

ዘጋቢ አብርሃም ጥላሁን
ፎቶ ግራፍ ብርሃን ገብሬ

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት
https://dfmc.mod.gov.et/

https://youtube.com/@fdredefenseforce-9629?si=Av-sDKCopw1FfTW2

https://t.me/+E_EOiTY9eq85ODI0

https://www.facebook.com/fdredefense.official
❤30👍12
August 30, 2026 4.1K