ብዙ የፖለቲካ ሞቶችን የሞተው ልደቱ አያሌው፣ እድሜውን ሙሉ በ«ሰላማዊ ትግል» መድረክ ሲንቀሳቀስ የኖረው፣ ዛሬ ላይ ተቀባይነት ለማግኘት ሲል ብቻ ቋሚ አቋሙን በመቀየር የትጥቅ ትግልን ለመቀላቀል ወይም ለመደገፍ ቢያስብም፣ ማንም ጆሮ የሚሰጠው አካል ጠፋ።
ቀጥሎም ራሱን እንደገና ለማዋቀር ከጀዋር ጋር የ«እንከራከር» ጥያቄ ቢጥልም፦ Jawar «ይህ የምርጫ ቅስቀሳ አይደለም፤ የ7ኛ ክፍል የአማርኛ ትምህርትም አይደለም» በሚል ፌዝ ተሳልቆበት አለፈ።
በፖለቲካው መስመር አንዳችም አዲስ መልክ መፍጠር ያልቻለው ይህ የዕድሜ ጠግብ ፖለቲከኛ፣ አሁን ደግሞ ፊቱን ወደ ሙዚቃ አዙሯል። እኔ የኪነ-ጥበብ ሰው ባልሆንም፣ ትንሽ አንዳንድ ዝንባሌዎች አሉኝ እና 'ሀሳብን በዜማ' የሚል 12 ዘፈኖችን የያዘ አልበም በ AI ሰርቻለሁ» በማለት አዲስ ትርኢት ይዞ ብቅ ብሏል። ከመስከረም 1 ጀምሮ ለ12 ተከታታይ ቀናት በየእለቱ አንድ ዘፈን እንደሚለቅ ተናግሯል።
እነ ቴዲ አፍሮ በኪነ-ጥበብ ላባቸውና በድምፃቸው ገበያውን ሞቀውት ሲወጡ፣ እርሱ ግን ኮምፒውተር አስነጥቆ «አርቲስት ሆንኩ» እያለ ነው። የኤርትራውያን 1.8 ሚሊዮን ዶላር የቀለም ወሬ እንዳለ ሆኖ፣ የልደቱ AI ዘፈን ደግሞ የአስመራን ቀርታ ትዝታ ሊያስነፍቀን ነው! 😢😂
ፖለቲካው ጨርሶ ስለተዘጋበት፣ ከዚህ በኋላ በዩቱብ ላይ ገበናውን እየነቀሰ ከማማት ይልቅ በ AI እየዘፈነ ዩቱብ ላይ መለፍለፉ ይሻለዋል። ቢያንስ የጡረታ ጊዜውን በዛው ራሱን እየጠጐረበት (እየተዝናናበት) ማሳለፍ ይችላልና መልካም የ«አርቲስትነት» ዘመን ይሁንለት! 😄
#ልደቱአያሌው #EthiopianPolitics #AIArt #EPRDF #EthiopianMusic #JawarMohammed #HabeshaHumor #SocialMediaPost #Ethiopia
—
Via Oromo Press Agency

4
3
2
2
1
1
1
1
1
1
1September 7, 2026 1K