በ| “የኦሮሞ ትግልና ታላቋ ኢትዮጵያ” ላይ አጭር የመጽሃፍ ዳሰሳ “የአሸባሪው ማስታወሻ” በሚለው የቀደመ… — 𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 — TG.ME

🔘|በ|  “የኦሮሞ ትግልና ታላቋ ኢትዮጵያ” ላይ አጭር የመጽሃፍ ዳሰሳ

“የአሸባሪው ማስታወሻ” በሚለው የቀደመ መጽሃፉ የምናስታውሰው ኦቦ ጋዲሳ አበራ፣ በቅርቡ ያሳተመውን አዲስ መጽሃፍ “የኦሮሞ ትግልና ታላቋ ኢትዮጵያ) አነበብኩት። ከመጽሃፉ አንዳንድ ነጥቦች አንስቼ እይታዬን ከማካፈሌ በፊት ደራሲውን ኦቦ ጋዲሳን መጽሃፉን ስለላከለኝ እጅግ አድርጌ ላመሰግነው እወዳለው።👀🙏

*

ይሄን ካልኩ ዘንዳ፣ መጽሃፉ ውስጥ ወደ ተነሱት አንዳንድ ነጥቦች ላምራና በስምምም ሆነ በሂሳዊ አካሄድ እየቀላቀልኩ ጥቂት አስተያየቶኦቼን ላስቀምጥ።
.

ኣ) የመጽሃፉ የይዘት ሽፋን አድማስ ከኦሮሞ ፖለቲካዊ ትግል ስረ መሰረት ተነስቶ፣ እስከታላቋ ኢትዮጵያ እውን መሆን ጽንሰ ሃሳብዊ ትንተና ድረስ የሚዘልቅ ነው። ደራሲው “ታላቋ ኢትዮጵያ” ሲል necessarily አሁን የምናውቃትን ኢትዮጵያ ሳይሆን፣ ተመሳሳይ/ተቀራራቢ የባህል፣ የታሪክና የፖለቲካል ኢኮኖሚ ፍላጎት ያላቸውን የምስራቅና የአፍሪካው ቀንድ አካባቢ ሃገሮችን ጭምር አስተሳስራ (integrate አድርጋ) የምትፈጠረውን ባለሰፊ ቁመትና ወርድ ባለቤት የምትሆነውን አዲስ ሃገር ይመስላል። ከዚህ አንጻር የቀረቡት ትንተናዎች መጽሃፉ ለአንባቢያን ያለውን ጠቀሜታ ከፍ ያደረጉ ሆነው ይታያሉ።

ባ) ደራሲው የኦሮሞን ትግል ስረ መሰረቶችና ስኬቶች እንዲሁም ተግዳሮቶችን ባቀረበባቸው የመጀመሪያዎቹ ዘጠኝ ምራፎች (መጽሃፉ ውስጥ ከተካተቱት ሃያ ሁለት ምራፎች አብዛኞቹ አጫጭሮች ናቸው)፣ በርካታ ውይይት የሚያጭሩ ጉዳዮችን ያነሳል። ለምሳሌ፣ የቀደሙት የኦሮሞ የትግል አባቶችና ያሁኖቹ ፖለቲከኞች ወይም አክቲቪስቶች የፖለቲካ ስልጣንን በተመለከተ ስላላቸው ከፍተኛ የእይታ ልዩነት በሚያቀርብበት ሶስተኛውና አራተኛ የመጽሃፉ ምራፎች ውስጥ የተነሱት ነጥቦች መሬት ጠብ የማይሉ ናቸው። ጉዳዮ በኦሮሞ ትግል ውስጥ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየታየ የመጣው ህዝባዊ ጥቅሞችን ሳይሆን የፖለቲካ ስልጣንን ማዕከል አድርጎ የማየት አባዜን (syndrom of political-power-centerism) በጥልቀት እንድናስተውል የሚጋዝብ ነው።

ቀደምቶቹ የኦሮሞ ትግል አባቶች የነበራቸውን ስልጣን እንኳን ትተው ህዝባዊ ወገንተኝነታቸውን በማሳየትና ህዝቡንም በማታገል ከፍተኛ የሞራል ልዕልናቸውን ያሳዩ ናቸው። በዚ ረገድ ከጀነራል ታደሰ ብሩ እስከ ጀነራል ዋቆ ጉቱ፣ ከኤሌሞ ቂልጡ እስከ ቄስ ጉዲና ቱምሳ እንዲሁም ከማሞ መዘምር እስከ ሃይሌ ፊዳ ያሉት ቀደምት የኦሮሞ ትግል አባቶች ያሳዩት ህዝባዊ ወገንተኝነትና ተምሳሌታዊ የሞራል ልዕልናቸው ተዳሷል።

በተቃራኒው ደግሞ ያሁኑ ፖለቲከኞች የኢትዮጵያ የፖለቲካ ስልጣን ተምሳሌታዊ ትዕምርት (symbolism for political power) መሆኑ የሚታወቀውን “አራት ኪሎ”ን ደረታቸውን ነፍተው “አታስለቅቁንም” ሲሉ ስንሰማ፣ በዚ ረገግ የጸሃፊውን የሰላ ትዝብት አግባብነት እንረዳለን።  በተቃዋሚ ጎራ ያሉትም ሆነ የገለልተኝነት ካባ ለብሰው “ ሴሌብሪቲ ሴሌብሪቲ“ የሚጫወቱት የፖለቲካ አክቲቪስቶችም የዚሁ ችግር ዋነኛ ሰለባ የመሆናቸው እውነታ ሊያከራክር አይችልም። ጽሃፊው በዚህ ላይም ብዙ ብሎበታል።

ጫ) ጸሃፊው “የኦሮሞ ትግል” በሚል ለበየነው የኦነግ የፖለቲካ ትግል እንቅስቃሴ ተገቢ እውቅናና ክብር በመስጠት ረገድ ፍትሃዊ እይታውን ካስቀመጠ በኋላ፣ ለኦነግ መዳከምና መከፋፈል ተጠያቀውን አካል በሚያፈላልግበት ስድስተኛው ምራፍ፣ የኦሮሞ ዲያስፖራን ለዚህ ተጠያቂ ያደርጋል።

በኔ እይታ የዚህ ዓይነቱ ድምዳሜ ላይ ለመድረስ ጠለቅ ያሉ ጥናቶችን ማካሄድ የሚፈልግ ቢሆንም፣ ኦቦ ጋዲሳ ከኦነግ ትግል ጋር ተያይዞ የኦሮሞ ዳያስፖራ ሚና ከሌሎች ሃገሮች የዳያስፖራ ማህበረሰቦች ጋር በታሪክ እያነጻጸረ የሚያቀርበው ሂስ ትኩረት የሚስብ ነው። እርሱ እንደሚለው በተለይም ከቻርተሩ ዘመን ማለትም ከ1991 በኋላ፣ በተለያዩ የምዕራብ ሃገሮች ያሉ የኦሮሞ ዳያስፖራ ማህበረሰቦች በተለይም በስነምግባር የለሽ ተግባራት (የኦሮሞ ትግል ውስጥ እንደተሳተፉ አስመስሎ በማጭበርበር በየሃገራቱ ወረቀት ማግኘትን ጨምሮ)፣ በሰርጎ ገብነት፣ መንደርተኝነትንና ጎሰኝነት (tribalism) ዓይነት ረብ የለሽ አስተሳሰቦችን በማስፋፋት፣ የመሪዎችን ስም አላግባብ በማጥፋትና ያልተገባ ተጽኖ በመፍጠር ወዘተ… በድርጅት ውስጥ እምነትን ቀስ በቀስ ሽርሽረው፣ የአመራር መዋቅሩ እንዳይረጋጋ ብቻም ሳይሆን እንዲፈርስ ጭምር አድርገውታል።

የኦነግ የፖለቲካ ትግል ላይ ለዶክትሬት ዲግሪ ጥናት እያካሄዱ ያሉ የቁቤው ትውልድ አባላት የሆኑ ምሁራን እንዳሉ አውቃለውና፣ ይሄ ኦቦ ጋዲሳ የሚያነሳው የዳያስፖራ ሚና ጉዳይም ወሳኝ ትኩረት የሚሻ መሆኑ በዚሁ አጋጣሚ መጠቆም ተገቢ ይመስለኛል። ለነገሩ ርዕሰ ጉዳይ ሰፋ ተሰርጎ፣ የአጠቃላይ ኢትዮጵያ የዳያስፖራ ማህበረሰቦች ሚና በፓርቲ ፖለቲካ እንዲሁም በሰላምና በሃገር ግንባታ ጋር ተያይዞ ጥናት ቢደረግ ጠቀሜታ ያለው ውጤት ሊገኝ እንደሚችል ጥርጥር የለውም።

ዳ) ጸሃፊው “የኦነግ ትግል: ተገቢው እውቅና የተነፈገው መስዋዕትነት” በሚለው ምራፍ ስር interesting የሆኑ ነጥቦችን ያነሳል። “በምስራቅ አፍሪካ ረጅሙ የፖለቲካ ትግል” የተባለው የኦነግ ትግል፣ መንግስታዊ ስልጣን ለመያዝ እድል ሳያገኝ ሃሳቦቹ ግን የኢትዮጵያን ሃገረ መንግስት ፖለቲካዊ ገጽታ መሰረታዊ በሆነ መልኩ እንደለወጠው ይከራከራል። እንደ ብሄራዊ እውቅና፣ ፌዴራሊዝም፣ የቋንቋ መብቶችና የባህል እኩልነት ያሉትን የፖለቲካ ትሩፋቶችን በመጠቃቀስ፣ እነዚህ ፍትሃዊ ትሩፋቶች ከኦነግ በፊት በነገረችው ኢትዮጵያ ፍጹም ሊታሰቡ የማይችሉ ስለመሆናቸው ይሞግታል። እነዚ የዛሬይቱን ኢትዮጵያ በመሰረተዊነት የበየኑ ፖለቲካዊ እሳቤዎች መጪም ሆኑ ሂያጅ መንግስታት ሊጥሏቸው የማይችሉ መሆናቸውን በማስረገጥ፣ ኦነግ በዚ ረገድ ላደረገው ታሪካዊ አስተዋጾ በቂ እውቅናና ክብር አላገኘም ባይ ነው ነጻፊው። ነጥብ ያለው ይመስለኛል።

ኤ) ደራሲው ኦቦ ጋዲስ አበራ፣ ከአስራ አንድ ዓመታት የፖለቲካ እስረኝነት ተለቆ ወደ ቄሮ ትግል የተቀላቀለበትን ሂደት የሚተርክበት ምራፍም የአንባቢን ትኩረት ሰቅዞ የሚይዝ ነው። ታሪኩ የኦሮሞን ትግል ስትራቴጂካዊ እድገትና ህዝባዊ አቅም (grassroots power) የሚያሳይም ነው ማለት ይቻላል።

እዚህ ላይ Hidhaan qoraasuma dhiiraati የሚለው የቆየ የኦሮሞ ታጋዮች አባባል ሊነሳ የሚገባው ነው። ሃሳቡ የተራዘመ ፖለቲካዊ የእስር ጊዜን ለንባብ፣ ለማሰላሰል እንዲሁም እንደጥሞና ጊዜ በመጠቀም፣ አስቸጋሪውን የእስር ቤት ኑሮ ለበጎ ነገር የማዋል አካሄድን የሚጠቁም ነው። ፈረንጆቹ a blessing in disguise እንደሚሉት ወይም አስከፊ በሆነ ነገር ውስጥም’ንኳ አንዳች በጎ ነገር ሊገኝ የመቻሉን እውነታ የሚገልጽ ጽንሰ ሃሳብ መሆኑ ነው።

ጸሃፊው ኦቦ ጋዲሳ፣ የቀድሞ ፖለቲካዊ አቋሞቹን የቀየረበትን ሂደት (ኦሮምያን ከኢትዮጵያ መገንጠል የሚለውን የበፊት አቋሙን ጨምሮ)፣ ከተራዘመ የእስር ቆይታው ከወጣ በኋላ በቄሮ ትግል ውስጥ በምን መልኩ መሳተፍ እንዳለበት የወሰነበት አካሄድ፣ እሱ በግልጽ ባያስቀምጠውም የዚሁ ህሳብ ተጋሪ መሆኑን አመላካች ሆኖ ይታያል።
❤2
September 7, 2026 310 1