ነገረ #ልደቱ
አቶ ልደቱ አያሌው ከርዕዮት ሚዲያ ጋር ያደረጉትን ቃለ ምልልስ ዘግይቼም ቢሆን ሰማሁት። ቴዲ ባለፈው ጀዋርን እንደዛ ሲያፈጥጠው ከልደቱም ጋር ተመሳሳይ ቆይታ ያደርጋል ብዬ ጠብቄ ነበር። ነገር ግን አልሆነም። ልደቱ አብዛኛውን ጊዜ ጀዋርን በማማት ነው ያሳለፈው ማለት ይቻላል። በእውነቱ፣ ልደቱ በዚህ መልኩ ቅንነትና ሐሳብ ነጥፎበት፣ character assassination ላይ ተሰማርቶ አይቼ አላውቅም። ጀዋርን በብዙ ነገሩ መተቸት እየቻለ ተራ ሀሜት ውስጥ መግባቱ አስገርሞኛል።
#ጀዋር በመንግሥት ጭምር ጥበቃ እንደሚደረግለትና ወደ እሱ ቤት የሚያቀና ማንኛውም ሰው እንደሚፈተሽ ብዙዎቻችን እናውቃለን። ይህ ከደህንነት አንጻር እንደሆነና ከክብር ጋር እንደማይገናኝ ልደቱ ቢስተው፣ ቴዲ እንዴት ዝም ሊለው ቻለ? በዚሁ አጋጣሚ፣ ወደ ጀዋር ቤት የሄዱ ሰዎች ነርቫቸው ለምን በዚህ ደረጃ እንደሚነካ የሆነ ጥናት ቢጤ ቢደረግ ባይ ነኝ😏
በነገራችን ላይ፣ ጀዋር በፖለቲካ ሕይወቱ ሁለት ግዙፍ ስህተቶችን ሠርቷል ብዬ አስባለሁ፤ በተለይም ከመታሰሩ በፊት።
አንደኛው፣ ኦፌኮን ተቀላቅሎ የአክቲቪስትነት ዘመን ነፃነቱን መገበሩ ሲሆን፤ ሁለተኛው፣ ልደቱን በኦኤምኤን ላይ ጋብዞ፣ ከመስከረም በኋላ “መንግሥት የለም” የሚል ዘመቻ ማስተጋባቱ ነበር። የሁለተኛው ጦስ፣ ከኮሮና ጋር ተዳምሮ፣ ለሐጫሉ መገደልና ለነጀዋር መታሰር አስተዋጽኦ እንደነበረው መካድ አይቻልም።
ልደቱ በዚህ ቃለ ምልልስ የራሱን ፖለቲካዊ ዋጋ ከፍ ለማድረግ የሞከረው አንዳንዴ አስቂኝ፣ ሌላ ጊዜ ደግሞ አደገኛ የሆኑ ፍረጃዎችን በመጠቀም ጭምር ነው። የኦሮሞ ሕዝብ በጀዋር ላይ የሚነሳው ልደቱ ስለተናገረ ብቻ አይመስለኝም። የሕዝቡን intelligence መናቅም ይሆናል። የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ጀዋር ላይ እንዲነሳ መቀስቀስም በራሴ ላይ ተደረገብኝ ከሚለው የግድያ አዋጅ የሚተናነስ አይደለም።
ጀዋር ፖለቲከኛ ነው። ፖለቲከኛ ዋነኛ ግቡ፣ በተገኘው አጋጣሚ ሥልጣን መያዝ ነው። በዚህ ስሌት፣ ጀዋር መፈንቅለ መንግሥት ቢያስብ ችግሩ ምንድነው? የኔ ለሚለው constituency ማለትም የኦሮሞ ሕዝብ ፍላጎት እንዲጠበቅ ቢታገልና ጽምዶ የዚህ ተቃራኒ ነው ብሎ ቢያስብ፣ መብቱ አይደለም ወይ?
አቶ ልደቱ ሆይ፣ እርሶ መንግሥተ ሰማያት ሊገቡበት ነው ፖለቲካ የሚሠሩት? እኔ ፖለቲከኛን በሚናገረው ሳይሆን፣ በሚፈጽማቸው ተግባራትና በድርጊቱ የምመዝን ሰው ነኝ።
ጀዋር ይህን ሥርዓት እንዳይወድቅ ቢከላከልና ኦሮሞ በቀጣይ ቦታውን ያጣል ብሎ ቢሰጋ፣ ኃላፊነት የሚሰማውና pragmatist የሆነ ፖለቲከኛ የሚያደርገው ነገር ነው ብዬ አስባለሁ። ለዚህ ስሜት ማረጋገጫ መስጠትና በመተማመን አብሮ መሥራት ሲገባ፣ በአደባባይ “ራቁቱን ቀርቷል” ብሎ መፎከር አግባብ አይደለም። በዚህ ሁኔታ ከአቶ ልደቱ ጋርስ ማን አምኖ ይሠራል? እኔ የታየኝ የጀዋር ራቁቱን መቅረት ሳይሆን፣ የአቶ ልደቱ ስጋትና ለሽንፈት የቀረበ አነጋገር ነው።
አንድ ነገር ግን ግልጽ ነው። ልደቱ በዚህ ንግግሩ ጽምዶ ገና በጠዋቱ መክሸፉን አውጇል። ከሌሎች ልሂቃን በተሻለ መልኩ የሰከኑና አማካይ መንገድ ሊጠቁሙ የሚችሉት እንደ ልደቱ ያሉ ሰዎች፣ በዚህ ደረጃ አንድን ትብብር፣ ለዚያውም ገና ፍሬው ያልታወቀውን፣ “ካልደገፍክ ትቀሰፋለህ” ካሉ እውነትም ችግር አለ ማለት ነው። ይህም ሀገርን ወደ ልማት ሳይሆን፣ ወደ ጥፋት የሚያመራ ነው የሚሆነው። ብቻ ሀገራችንን ሰላም ያድርግልን😊
VIA, [Hussein Tulu] 🙏🙏
.
.
3September 7, 2026 489