ዜና፦ በ #ትግራይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በ #ዓለም_ባንክ ድጋፍ የተገነባ የትምህርት ቤት የአይ ሲ ቲ (ICT) ማዕከል ወደመ
በትግራይ ክልል ሰሐርቲ ወረዳ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በዓለም ባንክ 3አር “3R” ፕሮግራም አማካይነት የተገጠሙ 35 ኮምፒውተሮችን የያዘው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ማዕከል መውደሙን የትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) አስታወቁ።
ዶ/ር ኪሮስ ባወጡት መግለጫ፣ ትምህርት ቤቱ ከ1999 ዓ.ም. ጀምሮ ከ500 በላይ ተማሪዎችን ሲያገለግል የቆየ እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ወሳኝ የትምህርት ማዕከል እንደነበር ጠቁመው፣ አሁን ግን የቴክኖሎጂ ማዕከሉ መውደሙን ገልጸዋል።
ኃላፊው በጥቃቱ ወቅት በአካባቢው «ምንም ዓይነት የወታደራዊ ዒላማ፣ ውጊያ ወይም የታጠቀ ኃይል እንቅስቃሴ አልነበረም» ያሉ ሲሆን፣ የፌዴራል መንግሥት በትምህርት መሠረተ ልማቶች ላይ ሆን ብሎ ጥቃት እያደረሰ ነው ሲሉ ከሰዋል።
https://addisstandard.com/Amharic/?p=13941

Addis standard
በትግራይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በዓለም ባንክ ድጋፍ የተገነባ የትምህርት ቤት የአይ ሲ ቲ (ICT) ማዕከል ወደመ - Addis standard
በአዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21/ 2018 ዓ.ም:- በትግራይ ክልል ሰሐርቲ ወረዳ በሚገኝ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ የድሮን ጥቃት በዓለም ባንክ 3አር “3R” ፕሮግራም አማካይነት የተገጠሙ 35 ኮምፒውተሮችን የያዘው የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ (ICT) ማዕከል መውደሙን የትግራይ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ኪሮስ ጉዕሽ (ዶ/ር) አስታወቁ። ዶ/ር ኪሮስ ባወጡት መግለጫ፣ ትምህርት ቤቱ ከ1999…
2August 27, 2026 996 1 1