የአሜሪካው ምስጢራዊ አገልግሎት (US Secret Service) የኢራን መንግስታዊ ብሮድካስተር የፕሬዝዳንት… — 𝐅𝐢𝐧𝐟𝐢𝐧𝐧𝐞𝐞 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬 — TG.ME

🚨 የአሜሪካው ምስጢራዊ አገልግሎት (US Secret Service) የኢራን መንግስታዊ ብሮድካስተር የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታናሽ ልጅ የሆነውን ባሮን ትራምፕን  ህይወት የሚያስፈራራ ቪዲዮ ማሰራጨቱን እንደሚያውቅና ጉዳዩንም እየመረመረው መሆኑን አስታወቀ ። በኢራን መንግስታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የተሰራጨው እና አካባቢዎችን የሚያሳየው ይህ ቪዲዮ የባሮን ትራምፕን እንቅስቃሴዎች እንደሚከታተል የሚገልጽ ሲሆን፣ ከቪዲዮው ጋር ተያይዞም የገንዘብ ወሮታ  የቀረበበት ዛቻ  አስተላልፎበታል።

የምስጢራዊ አገልግሎቱ ቃል አቀባይ “የአሜሪካ ምስጢራዊ አገልግሎት ስለ ቪዲዮው እውቀቱ ያለው ሲሆን፣ በእኛ ጥበቃ ስር ባሉ ሰዎች ላይ የሚሰነዘርን ማንኛውንም አይነት ስጋት መርምሮ እርምጃ ይወስዳል” ብለዋል። ቀደም ሲል በኢራን ሚዲያዎች በራሱ በፕሬዝዳንት ትራምፕ እና በቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕ ላይ ተመሳሳይ የማስፈራሪያ ቪዲዮዎች ተሰራጭተው የነበረ ቢሆንም፣ ልጃቸውን ባሮን ትራምፕን በቀጥታ ያላመደ የማስፈራሪያ ቪዲዮ ሲወጣ ግን ይህ የመጀመሪያው ነው።

Source #CNN


https://t.me/Brics4ethiopia/5948
Telegram
BRICS 𝐏𝐫𝐞𝐬𝐬
🚨 የአሜሪካው ምስጢራዊ አገልግሎት (US Secret Service) የኢራን መንግስታዊ ብሮድካስተር የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ታናሽ ልጅ የሆነውን ባሮን ትራምፕን ህይወት የሚያስፈራራ ቪዲዮ ማሰራጨቱን እንደሚያውቅና ጉዳዩንም እየመረመረው መሆኑን አስታወቀ ። በኢራን መንግስታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ የተሰራጨው እና አካባቢዎችን የሚያሳየው ይህ ቪዲዮ የባሮን ትራምፕን እንቅስቃሴዎች እንደሚከታተል የሚገልጽ ሲሆን፣…
❤2
August 25, 2026 746