የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተናን 591.6 በማምጣት በኢትዮጵያ ቀዳሚ የሆነው ተማሪ ጃለል ግርማ ታሪካዊ ስኬት
#FastMereja I በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተማሪ ጃለል ግርማ 600 ከተያዘው ሙሉ ነጥብ 591.6 በማስመዝገብ ከሀገሪቱ ተፈታኞች በሙሉ የላቀውንና ቀዳሚውን ውጤት በማስመዝገብ ታሪክ ሰርቷል።
ትውልዱ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ጃርሶ ወረዳ የሆነው ተማሪ ጃለል፣ ከዘጠነኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያለውን ትምህርቱን በሕዝብ ድጋፍ በሚንቀሳቀሱት በቢሾፍቱ እና በአዳማ የኦዳ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ሲከታተል ቆይቷል። ከመዋዕለ ሕፃናት ጀምሮ በከፍተኛ ውጤቱና ለትምህርት ባለው ልዩ ፍቅር የሚታወቀው ይህ ወጣት፣ ለዚህ ዘላቂ ስኬት የበቃው በራሱ ጠንካራ ትጋት፣ ባልተቋረጠ የቤተሰብ ክትትል እንዲሁም በመምህራንና በህዝቡ ያልተቆጠበ ድጋፍ መሆኑን ገልጻል።
ወደፊት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተፈላጊነት ባለው የሰው ሰራሽ አስተውሊት (AI) ዘርፍ ትምህርቱን በመቀጠል ሀገሩንና ህዝቡን ለማገልገል ማቀዱን የተናገረው ተማሪ ጃለል፣ የካበተ የማንበብ ልምዱ ለውጤቱ መመዝገብ ትልቅ አስተዋጽኦ ማበርከቱን አባቱ አቶ ግርማ ኩሳ አረጋግጠዋል። የኦሮሚያ ልማት ማኅበር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ አባዱላ ገመዳ በበኩላቸው፣ የተገኘው ውጤት መንግሥትና ህዝብ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና የልህቀት አዳሪ ትምህርት ቤቶችን በመገንባት ያደረጉት ጥረት በተጨባጭ ፍሬ ማፈራቱን የሚያሳይ መሆኑን ተናግረዋል ሲል ኢቢሲ ነው የዘገበው።
6
2August 29, 2026 4.1K 1