FACE THE TRUTH: post #367 — TG.ME

እግዚአብሔር  በትግል ተሸንፎ ያውቃል

🔘 መፅሐፍ ቅዱስ ላይ እንደተፃፈው እግዚአብሔር ከያዕቆብ ጋ ለሊት ሙሉ ሲታገል እንደነበር እና ቆይቶ በመጨረሻ  ግን ያዕቆብ እንዳሸነፈው መፅሐፍ ቅዱስ ይናገራል።

📕ዘፍጥረት 32:24-27
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁴ ያዕቆብ ግን ለብቻው ቀረ፤ አንድ ሰውም እስከ ንጋት ድረስ ይታገለው ነበር።
²⁵ እንዳላሸነፈውም ባየ ጊዜ የጭኑን ሹልዳ ነካው፤ ያዕቆብም የጭኑ ሹልዳ ሲታገለው ደነዘዘ።
²⁶ እንዲህም አለው፦ ሊነጋ አቀላልቶአልና ልቀቀኝ። እርሱም፦ ካልባረክኸኝ አልለቅቅህም አለው።
²⁷ እንዲህም አለው፦ ስምህ ማን ነው? እርሱም፦ ያዕቆብ ነኝ አለው።
²⁸ አለውም፦ ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ እስራኤል ይባል እንጂ ያዕቆብ አይባል፤ ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና።

🌐 ያዕቆብ ስሙ እስራኤል የተባለው ከእግዚአብሔር ጋ ታግሎ ስላሸነፈ መሆኑ ቁጥር 28 ላይ በግልፅ ተቀምጧል።


🔘 የፕሮቴስታንት ምሁራንን ማብራሪያ ብታዩ ዘፍጥረት 32:24ን ሲያብራሩ
ነገሩ Christophany እንደሆነ ይናገራሉ።
ለምሳሌ Joseph Benson ሲያብራራ ያዕቆብ ሲታገል የነበረው ሰው የእግዚአብሔር ልጅ ዘላለማዊ ቃል በሰው መልክ ተገልጦ እንደሆነ ይናገራል።ዞሮ ዞሮ ያ ሲታገል የነበረው ኢየሱስ ተገልጦ ከነበረ ለውጥ አይፈጥርም ያው ኢየሱስ ተሸነፈ ነው የሚሆነው ።


✍️ Abdulkerim

https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
😁225👍50❤27😱10🔥6👏6🤩3💯3😭3🤯2
August 28, 2026 5.3K 33