🔘 ምን እያለን ነው ይህ ክርስቲያን ሰባኪ
የክርስቲያን ወገኖቻችን ጤና ከእለት እለት እያሳሰበኝ ነው ። ፈጣሪያችሁ ድካም አለበት ተፈጥሮ ላይ ጥገኛ ነው ሲባሉ ነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ ) ድካም አለባቸው ምግብ ይበላሉ ብለው ይገረማሉ። ነብይ ምግብ አይበላም ነው ? ምን እያልከን ነው ? ሁሌ ይመጡና አምላካችን የሚሉትን አካል ከነብዩ (ሰዐወ) ጋ በማወዳደር ሲያወሩ ይገርመኛል ። እኛ ነብዩ ሙሐመድ (ሰዐወ) ፈጣሪ ናቸው መች አልን ::
ይመጣና ሙሐመድ ሞቷል ኢየሱስ ግን ሞቶ ከዛ ተነሳ ይልሃል ። Bro እኛኮ ከመነሻው አምላካችንን ጭራሽ የማንፈልግበት ቦታ መቃብር መንደር ነው። ጭራሽ መቃብር መንደር ገብተን ሙታንን አወዳድረን ለአምላክነት እንሹም ?? ምግብ መብላት አየር መተንፈስ መሞት .... እነዚህ ሁሉ ተፈጥሮ ላይ ጥገኛ እና ተፈጥሮ በዛ አካል ላይ የበላይነት እንዳላት የሚያረጋግጥ ነው።
ለዛ ነው አምላካችን አላህ በተከበረ ቃሉ በቁርዓን ላይ በማይሞተው በአላህ ተመኩ እያለ ሌላው ሁሉ በተፈጥሩ ስር መሆኑን እሱ ብቻ ምንም ነገር የማይሰለጥንበት መሆኑን የነገረን።
📕 ቁርዓን ምዕራፍ 25:58
وَتَوَكَّلْ عَلَى الْحَيِّ الَّذِي لَا يَمُوتُ وَسَبِّحْ بِحَمْدِهِ ۚ وَكَفَىٰ بِهِ بِذُنُوبِ عِبَادِهِ خَبِيرًا
በዚያም በማይሞተው ሕያው አምላክ ላይ ተመካ፡፡ ከማመስገንም ጋር አጥራው፡፡ በባሮቹ ኀጢኣቶችም ውስጠ ዐዋቂ በእርሱ በቃ፡፡
አላህ ሂዳያ ይስጣችሁ !!
✍️ Abdulkerim
https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
365
197
96
21
11
11
7
5
4
3
2June 20, 2026 26.3K 44