FACE THE TRUTH: post #309 — TG.ME

🔘ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ  እነሱ ራሱ አልገባቸውም ። አስተማሪዎቻቸው እንኳን ሳይገባቸው ነው የሚኖሩት ።

🌠 የሚጨቃጨቁበትን ጉዳይ  ልንገራችሁ
ኢየሱስ በማቴዎስ ወንጌል ላይ ስልጣን ተሰጠኝ በማለት ስልጣን እንደተቀበለ ይናገራል ።

📕 ማቴዎስ 28፥18
“ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ ብሎ ተናገራቸው፦ ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ።”

🔘 አሁን ጥያቄው ኢየሱስ አምላክ ከሆነ  እንዴት ይቀበላል ነው  ?

🌐 አንደኛው መምህር (ነጠላ የጠመጠመው)

ኦርቶዶክስ ነው።
ኢየሱስ ማለት 100% የሰው ባህሪ  ሲደመር 100% የአምላክ ባህሪ  = ከሁለቱ የተዋሃደ 1 ባህሪ ብሎ ነው የሚያምነው ።ለዛ ኢየሱስ ስልጣን ተቀበልኩ ሲል በሰውነቱ ነው እያለ ያለው ነው

🌐 ሌላኛው መምህር  ደግሞ  (ጥቁር ጃኬት ያደረገው )

ኢየሱስ ተቀበልኩ ሲል በመለኮቱ ነው ነገር ግን ይህ መለኮቱ ወደ ምድር ሲመጣ  አምላክነቱን ትቶት ነው የመጣው  ለዛ ነው ተቀበልኩ የሚለው እያለ ነው። መጨረሻ ላይ ከሰማችሁት ይህ ካልገባህ ወንጌል አልገባህም አለው 😁

🌠 አንተ ምን ትላለህ ካላችሁኝ ለጭቅጭቅ የዳረጋቸው ነገር መጀመሪያ ያለ መረጃ የተቀበሉት ነገር አለ ሁለቱም።

ኢየሱስ ለራሱ ያልሰጠውን ምንነት ሰጥተህ አምላክ ነው ብለህ እሱ ያላስቸማውን ነገር ይዘህ ከገባህ ስልጣን ተሰጠኝ ምናምን ሲል አምላክ ነው ብለህ የተሸከምከው ሀሳብ ሊወድቅ ይንገዳገዳል ።ስለዚህ  አንድ ውሸት ሁሌም ሌላ ውሸት ስለሚፈልግ ሀሳቡ እንዳይወድቅ ሌላ ውሸት መጨመር ያስፈልጋል። ሁለተኛው ውሸት ላይ ነው መስማማት አቅቷቸው ነው የሚከራከሩት።


   ✍️ Abdulkerim

https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
👍191😁128❤58🫡8😱6🙈5🎉3
June 14, 2026 23.9K 27