የሙስሊሞች የተሳሳተ የተቃውሞ መንገድ እኛ ሙስሊሞች የማንንም ንፁህ ሰው ሞት እንቃወማለን እናወግዛለን ።… — FACE THE TRUTH — TG.ME

የሙስሊሞች የተሳሳተ የተቃውሞ መንገድ

እኛ ሙስሊሞች የማንንም ንፁህ ሰው ሞት እንቃወማለን  እናወግዛለን ። አርሲ የደረሰውን ሞት እንቃወማለን ነገር ግን የምትቃወሙበትን መንገድ አስተካክሉ

ዘለህ ኦርቶዶክስ ተገፋች ተገደለች  ተጨቆነች  አትበል ! አክሱም ላይ በሰላም ለመኖር ተውና  ለመሞት እንኳት አትቀበሩም ታረክሳላችሁ በማለት ሙስሊሞችን ረግጠው ያሉት እነማን ሆኑና ? ራሳቸው ኦርቶዶክስዎች ናቸው። የአርሲ ንፁሃንን ሞት  ብቻ ነጥለህ ተቃወም !  የንፁሃን ደም መፍሰስ የለበትም ።

ከዚህ ባለፈ የፖለቲካቸው ከበሮ በተደለቀ ቁጥር እየጮህክ የኦርቶዶክስ የፖለቲካ መስሪያ ድምፅ አትሁን።

🌐 ለመቃወም ከፈለክ በምን መልኩ እንደምትቃወም  2 ናሙና ልስጥህ

ናሙና 1️⃣
"በአርሲ የደረሰውን የንፁሃን ሞት እና በአክሱም ሙስሊሞች ላይ ኦርቶዶክስ የምታደርሰውን ስቃይ እቃወማለሁ "

ናሙና 2️⃣
" ለአክሱም ሙስሊሞች ስቃይ እና ለአርሲ ንፁሃን ሞት መንግስት ዘላቂ መፍትሔ እንዲሰጠን እንጠይቃለን "


ከላይ ያሉትን ናሙናዎች  መንገዱን ላሳያችሁ እንጂ በተሻለ መልኩ ፅፋችሁ ሀሳባችሁን መግለፅ ትችላላችሁ ።


   ✍️ Abdulkerim

https://t.me/Facethetruth22
------------------------------------------------------
👍350🔥160❤59👏31💯14🥰11🫡4🆒3
June 3, 2026 20.5K 13