ከጭንቀት_ለማምለጥ ከዕለታት ባንዱ ቀን...በዚህች ዓለማዊ ህይወት ሃሳብና ጭንቀት የተጨናነቀ ሰው ወደ አንድ… — ፒያሳ መሀሙድ ጋ ጠብቂኝ — TG.ME

ፒያሳ መሀሙድ ጋ ጠብቂኝPhoto
#ከጭንቀት_ለማምለጥ

ከዕለታት ባንዱ ቀን...በዚህች ዓለማዊ ህይወት ሃሳብና ጭንቀት የተጨናነቀ ሰው ወደ አንድ ጥበበኛ አዛውንት ጋር መጣ። እናም እንዲህ ተወያዩ......

ባለ ጉዳዩ ፡- “ ወደ እርሰዎ ዘንድ የመጣሁት ካለሁበት የህይወት አጣብቂኝ መውጣት የምችልበትን መፍትሄ ፈልጌ ነው ። ”

ጠቢቡ ፡- “ ሁለት ጥቄዎችን ልጠይቅህ እሻለሁ ። ”

ባለ ጉዳዩ ፡- “ ይጠይቁ ! ”



ጠቢቡ ፡- “ ወደ ዚህች ዓለም ስትመጣ አሁን ከተጋረጠብህ ችግር ጋር አብረህ ነው  የመጣኸውን ? ”

ባለ ጉዳዩ ፡- “ ኧረ በፍፁም  ! ”

ጠቢቡ ፡- “ጥሩ❗️ ይህችን ዓለምስ ተሰናብተህ ስትጓዝ አሁን የተጋረጠብህን የችግር  ጠቅልለህ ነው እንዴ የምትሄደው ? ”

ባለ ጉዳዩ ፡- “ አይደለም ”

ጠቢቡ ፡- “ ካንተ ጋር አብሮ ያልመጣ እና አብሮህ የማይጓዝ ችግር ይህን ሁሉ ሃሳብና ትካዜ ሊያወርስህ ተገቢ አይደለም ።.....

ጠቢቡ ትንሽ ካሰላሰሉ በኋላ...."ሰማኸኝ የኔ ልጅ....

👉በምድራዊ ጉዳይ ታጋሽ መሆን ይጠበቅብሃል ። ያሻኸውን ታገኝ ዘንድ እይታህን ወደ መሬት ከምታደርገው በረዘመ መልኩ ወደ ሰማይ አሻግረው ።

አሁንም በተመስጦ ተሞልተው "እምምምም.." ካሉ በኋላ

👉 ልጄ ሲሳይህ የተወሰነ ነው …

👉"ላንተ ነው !"የተባለውን አንተ ብቻ ነህ የምታገኘው …

👉ላንተ ያልሆነው ፈፅሞ ያንተ አይደለም ።

ትንሽ በአትኩሮት ካሰላሰሉ በኋላ.....

👉 ልጄ ሆይ ምድርን የምትሰናበተው አንተ በፈለከው ጊዜ ሳይሆን እርሱ በወሰነው ወቅት ነው ።

👉ህይወት ህያው እና ሃያል በሆነ ፈጣሪ ቁጥጥር ስር ሆና ሳለ ያንተ በትካዜ መቆራመድ ፋይዳ የለውም ።

👉ሲሳይህ የሚሰፈረው በሰው እጅ ሳይሆን የሲሳይ ጎተራው ልኬት በሌለው ፈጣሪ ነው ።

👉ትላንትን የኖርክበት የህይወት ቀመር ትርፉ ስቃይ ብቻ ከነበረ ዛሬ የምትኖርበትን የህይወት ቀመር ለውጠው ።

......ትንሽ በአትኩሮት ዐይናቸውን ከጣሉበት በኋላ......

👉 የኔ ልጅ ከመሳቀቅ በፈጣሪህ መመካት ይሻላልና ተመካ !!!".......ሲሉ መከሩት❗️

#Share
#Share #Share
#ከወደዱት like👍 እና share እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል፡፡

🚨በYouTube አማራጭ ይቀላቀሉን

❇️SUBSCRIBE NOW👇👇👇
https://youtu.be/Eb7GSEtReo0?si=xnW1Fqjr0ezyZ2xo

መልካም ቀን ተመኘሁ🙏

❇️ግሩፑን ለማግኘት
          👇👇

https://t.me/Mtshaf_bicha
https://t.me/piyasa188
   
🙏አሰተያየት ካላችሁ👇
                      @Eyos18  አድርሱን
📚ማንበብ ባህላችን ይሁን📚
┄┉┉✽‌»‌🎶••✿••🎶»‌✽‌┉┉┄
YouTube
🛑ዘዳቬንቺ ኮድ [#ክፍል 12]
#ተከታታይ የመፅሐፍ ትረካዎች
❤32👍3👎2👏1
June 14, 2026 9.2K 22