የፖርቹጋል ብሔራዊ አሰልጣኝ ሮቤርቶ ማርቲኔዝ ከዓለም ዋንጫ በኋላ ከሃላፊነታቸው እንደሚለቁ ተሰማ።
የ52 ዓመቱ ስፔናዊ አሰልጣኝ ኮንትራቱ በዚህ ውድድር ማብቂያ ላይ የሚጠናቀቅ ሲሆን፥ ፖርቹጋል በሰሜን አሜሪካው የዓለም ዋንጫ ላይ የምታመጣው ውጤት ምንም ይሁን ምን ኮንትራቱን ላለማደስ ወስኗል።
ማርቲኔዝ እ.ኤ.አ. በጥር 2023 የፈርናንዶ ሳንቶስን ቦታ ከተረከበ በኋላ እንደ ክሪስቲያኖ ሮናልዶ፣ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እና በርናርዶ ሲልቫ ያሉ ኮከቦችን የያዘውን ድንቅ ትውልድ ሲያሰለጥን ቆይቷል። አሰልጣኙ በቤልጂየምና ፖርቱጋል የብሄራዊ ቡድን ሀላፊነት ለ10 አመታት ከቆየ በኋላ ወደ ክለብ አሰልጣኝነት ለመመለስ ፍላጎት እንዳለው ተገልጿል።
ማርቲኔዝ ቀደም ሲል ስዋንሲ፣ ዊጋን እና ኤቨርተንን አሰልጥኗል።አሁን ላይ ግን ሙሉ ትኩረቱ ፖርቹጋልን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫ ባለቤት እንድትሆን ማድረግ ላይ እንደሆነ ተገልጿል።
ፖርቹጋል በምድብ 11 የመጀመሪያ ጨዋታዋን ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር አድርጋ 1 ለ 1 መለያየቷ ይታወቃል።
1June 18, 2026 594

