አወዛጋቢው ሴዶ ማርሻል..‼️
«እንቁላሉን አክሽፌ Cage ውስጥ እገባለሁ!» — ሴዶ ማርሻል ውሳኔውን ቀየረ
በETFC 2 Cage ውድድር ላይ ከግጥሚያው ራሱን ለማግለል ወስኖ የነበረው የMMA ተወዳዳሪ ሴዶ ማርሻል፣ ውሳኔውን በመቀየር ወደ Cage ለመግባት መወሰኑን አስታዉቋል።
ሴዶ በአዲስ ቪዲዮ ላይ የህዝቡን ጉጉትና ፍላጎት ካየ በኋላ ውሳኔውን መቀየሩን ገልጿል። በተጨማሪም፣ «በእንቁላሉ የተሰራውን መተትና ድግምት አክሽፌ ለህዝቡ ስል Cage ውስጥ እገባለሁ» ብሏል።
ንግግሩንም በተግባር ለማሳየት በእጁ የያዘውን እንቁላል ሰብሮ «ቢስሚላህ» በማለት ጠጥቶታል።


















