ለሜሲ ክብር ለአንድ ደቂቃ ጨዋታ ይቋረጣል !
የአርጀንቲና ሊጎች በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረጉ ጨዋታዎች ላይ ለሊዮኔል ሜሲ ያላቸውን ክብር ያሳያሉ።
በቀጣይ የሚደረጉ መርሐ ግብሮች የጨዋታው 10ኛ ደቂቃ ላይ ለአንድ ደቂቃ እንደሚቋረጡ ተገልጿል።
በሁሉም የአርጀንቲና የሊግ እርከኖች ላይ እንደሚተገበር የሀገሪቱ እግርኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ይህ የሚሆነው ለታሪካዊ ተጨዋቻቸው ሊዮኔል ሜሲ አክብሮት ለማሳየት መሆኑ ተገልጿል።

September 2, 2026 110