2-step verification ምንድን ነው? እንዴትስ እንጠቀመዋለን?
እንደሚታወቀው በማንኛውም website ወይም application ላይ account ከከፈትን በኋላ username እና password አስገብተን login ማድረግ እንችላለን። ነገር ግን username እና password ብቻውን አስተማማኝ ስላልሆነና ለ3ኛ ወገን ተጋላጭ ስለሚያደርገን ብዙ ድርጅቶች ተጨማሪ የsecurity step ይጨምራሉ። ስለዚህ ሃከሩ ዩሰርኔምና እና ፓስዎርዳችን ቢኖረው ራሱ login ለማድረግ ተጨማሪውን step ማለፍ ይጠበቅበታል። ይህ ተጨማሪ ሁለትም ሆነ ከዛ በላይ security feature 2-step verification ይባላል። ከ2 በላይ ከሆነ ደግሞ multi step verification/authentication ይባላል።
ይህም የsecurity ደረጃውን ከፍ ለማድረግና access የሚያደርገው ትክክለኛ ባለቤቱ መሆኑን ለማረጋገጥ ያግዛል።
አሁን አሁን ሁሉም ሶሺያል ሚዲያዎች ማለት ይቻላል 2-step/multi step verification አላቸው። ስለዚህ ያሉንን ሶሻል ሚዲያዎች 2 step verification "on" ማድረግ አለብን።

1November 20, 2024 444