አንድ AI ብቻ መጠቀምህን አቁም! ChatGPT አንድ መልስ ሰጠህ… ትክክል ነው? ስህተት ነው? የተሻለ… — EthioRise Tech — TG.ME

🔥 አንድ AI ብቻ መጠቀምህን አቁም!
ChatGPT አንድ መልስ ሰጠህ…
ትክክል ነው?
ስህተት ነው?
የተሻለ አማራጭስ አለ?
አንተ አታውቅም። 😳
እኔ ዛሬ ግን በጣም አስገራሚ የAI አጠቃቀም ላሳይህ።
የራስህን “AI Board of Directors” ፍጠር! 🤯
ለምሳሌ አንድ Business Idea አለህ እንበል።
🤖 AI #1 — The Creator
ChatGPTን፦
“ይህን idea ተንትነህ ምርጥ business plan ስጠኝ።”
ትለዋለህ።
Plan ይሰጥሃል።
ግን እዚያ አታቁም!
የሰጠህን Plan copy አድርገህ…
🧠 AI #2 — The Critic
ለClaude ስጠውና፦
“ይህን Plan አትደግፈው።
ሊያስከስረኝ የሚችለውን፣ ያላሰብኩትን፣ weak assumptions እና hidden risks ፈልግልኝ።”
በለው። 😈
Claude የመጀመሪያው AI ያላየውን ችግር ሊያሳይህ ይችላል።
ከዚያ…
💎 AI #3 — The Judge
Plan + Criticism ሁለቱንም Gemini ላይ አስገባና፦
“ሁለቱንም ተንትን።
የማይሰራውን አስወግድ፣
ጠንካራውን አስቀር፣
ከዚያ የተሻለ Final Plan ገንባልኝ።”
በለው። 🔥
አሁን ምን አደረግክ?
❌ AIን እንደ Google አልተጠቀምክም።
AIዎችን እርስ በርስ አከራከርክ! 😳
አንዱ ፈጠረ።
ሁለተኛው ቀዳዳውን ፈለገ።
ሦስተኛው ሁለቱን ተንትኖ አሻሻለ።
🚨 ግን ዋናው SECRET ይሄ ነው፦
ሦስቱም AIዎች ሊሳሳቱ ይችላሉ።
ሦስቱ ተስማሙ ማለትም ነገሩ እውነት ሆነ ማለት አይደለም።
ስለዚህ…
👑 Final Decision የማን ነው?
ያንተ!
AI #1 → ይፍጠር
AI #2 → ይቃወም
AI #3 → ያሻሽል
አንተ → አስብ፣ አረጋግጥ፣ ወስን።
ይሄን Business ብቻ ሳይሆን፦
📚 ትምህርት
💻 Programming
💼 Career decisions
📊 Project planning
✍️ Content creation
🔍 Research
ላይም መጠቀም ትችላለህ።
🔥 AIን መጠቀም ብቻ አትማር።
AIን እንዴት ማስተዳደር እንዳለብህ ተማር።

🚀 @EthioRiseTech | Technology With Purpose
👏6🤔1🤩1
October 6, 2026 124 2