Ethio_E_learning_center_Grade 9-10: post #571 — TG.ME

በአፋር ክልል 759 ትምህርት ቤቶች አሸባሪው የህወሃት ቡድን ባደረሰው ጥቃት ወድመዋል ============================= በክልሉ በአራት ዞኖችና 21 ወረዳዎች የሽብር ቡድኑ ባደረሰው ጉዳት 694 ትምህርት ቤቶች በከፊል፣ 65 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ በድምሩ 759 ትምህርት ቤቶች ወድመዋል። የአፋር ብሔራዊ ክልል መንግስት ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ መሐመድ የወደሙትን ትምህርት ቤቶች መልሶ ለመገንባትና የትምህርት ሥራውንም ለማስቀጠል በክልሉ ከተለያዩ ዘርፎች የተውጣጡ ባለድርሻ አካላትንና አመራሮችን ባካተታ መልኩ የተዋቀረ ቡድን ወደ ሥራ መግባቱን በመጥቀስ ለመልሶ ጥገናውና ግንባታው የሚያስፈልገው አጠቃላይ ወጪ ተሰልቶ በቅርቡ ይፋ እንደሚሆንም ገልጸዋል። የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ በመጠገንና በመገንባት የትምህርት አገልግሎትን ከማስቀጠል አንፃር ህብረተሰቡ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል። የጭፍራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ መሐመድ አብዱ በበኩላቸው የትምህርት ቤቶቹ የጉዳት መጠን ሲታይ በተለይ በአፈጻጸማቸው ሞዴል በሆኑትና በአንጋፋ ትምህርት ቤቶች ላይ የከፋ መሆኑን ጠቅሰው ይህ ድርጊት ወራሪው ሃይል ለአፋር ህዝብና ልጆች ያለውን የጠላትንት ጥግ ያሳየ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

👍2👎1
December 29, 2021 7.5K 1