በሳይት ላይ የSelect Material ጥራት ቁጥጥር! ​በምስሉ ላይ እንደምናየው ለመሰረት… — SMH General Construction — TG.ME

በሳይት ላይ የSelect Material ጥራት ቁጥጥር!

በምስሉ ላይ እንደምናየው ለመሰረት (Backfilling) ወይም ለመንገድ ሰብ-ቤዝ (Sub-base) የሚያገለግል የሴሌክት ማቴሪያል (Select Material) ክምችት እናያለን። ይህ ማቴሪያል ከፋውንዴሽን በላይ ወይም በሰላብ ስር ለሚሞላው አፈር ጠንካራ መሰረት ለመፍጠር ያገለግላል።

​ጥራት ያለው Select Material 3 ዋና ዋና ባህሪያት፦

1. ​Well-Graded Mixture (የተመጣጠነ ስብጥር)፦ በትልልቅ ድንጋዮች መካከል ያሉትን ባዶ ቦታዎች (Voids) የሚደፍን በቂ ደቃቅ አሸዋ/አፈር እና ጠጠር ስብጥር ሊኖረው ይገባል።

2. ​Low Plasticity Index (PI < 6-10%)፦ ከፍተኛ የሸክላ አፈር (Clay) ስብጥር ሊኖረው አይገባም፤ ምክንያቱም ውሃ ሲያገኝ የማበጥ እና የመኮማተር (Swelling & Shrinkage) ባህሪ ስለሚያሳይ።

3. ​Free from Organic Matter፦ ከአረም፣ ከዕፅዋት ስሮች እና ከቆሻሻ ሙሉ በሙሉ የጸዳ መሆን አለበት።

​በእርስዎ ሳይት ላይ ሴሌክት ማቴሪያል ከተደፋ በኋላ በየስንት ሴንቲሜትር (cm) ንብርብር (Layer) አድርገው በኮምፓክተር ያስመታሉ? (15cm ወይስ 20cm?) ሃሳብዎን በኮሜንት ያካፍሉን!


https://t.me/ethioengineers1
❤25
August 22, 2026 4K 14