የስላብ ብረት (Slab Rebar Work) በሚታሰርበት ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ዋና ዋና ጥንቃቄዎች! ​የስላብ… — SMH General Construction — TG.ME

🏗️ የስላብ ብረት (Slab Rebar Work) በሚታሰርበት ወቅት ሊደረጉ የሚገቡ ዋና ዋና ጥንቃቄዎች!

የስላብ ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት የብረት ማሰር ስራው በህንፃው ጥንካሬ እና ደህንነት ላይ ቀጥተኛ ተፅዕኖ አለው። በሳይት ላይ የቁጥጥር ስራ ስናደርግ ትኩረት ልንሰጣቸው የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

1️⃣ Spacer Blocks (ኮንክሪት ከቨር): ብረቶቹ ከፎርምወርክ (Formwork) እንጨት ጋር እንዳይነካኩ እና ከስር በቂ የኮንክሪት ሽፋን (Concrete Cover) እንዲኖራቸው ኮንክሪት ወይም ፕላስቲክ ስፔሰሮችን መጠቀም።

2️⃣ Bar Spacing & Overlap (የብረት ርቀት እና ማያያዣ): በዲዛይኑ መሰረት በብረቶች መካከል ያለው ርቀት (Spacing) በትክክል መጠበቁን እና የብረት ማያያዣ (Lap Length) ርዝመት በቂ መሆኑን ማረጋገጥ።

3️⃣ Binding Wire (የማሰሪያ ቢያንኮ): እያንዳንዱ የብረት መገናኛ (Intersection) በሚገባ በማሰሪያ ቢያንኮ መታሰሩን ማረጋገጥ—ኮንክሪት ሲሞላ ብረቱ ቦታውን እንዳይቀይር።

4️⃣ Top & Bottom Mesh (የላይኛ እና የታችኛ ብረት): ድብል ሜሽ (Double Mesh) በሚሆንበት ጊዜ በሁለቱ ሜሾች መካከል ያለው ርቀት እንዳይጠበብ ወንበር/ቼር (Chairs) መጠቀም።

5️⃣ የፅዳት ስራ (Site Cleaning): ኮንክሪት ከመሞላቱ በፊት በፖሊቲን/ፕላስቲክ (Polythene sheet) ላይ ያሉ የዛፍ ቅጠሎች፣ የቢያንኮ ቁራጮች እና አቧራዎች በሚገባ መጽዳት አለባቸው።

https://t.me/ethioengineers1
❤17👍1
August 22, 2026 3.3K 13