በሳይት ላይ የPad Footing PVC Sleeves Inspection! 🧐🏗️ ​በምስሉ ላይ እንደሚታየው… — SMH General Construction — TG.ME

በሳይት ላይ የPad Footing PVC Sleeves Inspection! 🧐🏗️

​በምስሉ ላይ እንደሚታየው የፓድ ፉቲንግ ኮንክሪት ከተፈሰሰ በኋላ በስታርተር ብረቱ ዙሪያ የPVC ቱቦዎች (Sleeves) ተተክለው ይገኛሉ። ይህ አሰራር በስራ ቦታዎች ላይ ለተለያዩ ኢንጂነሪንግ ዓላማዎች ይውላል።

​በፉቲንግ ላይ PVC Sleeves የሚተከሉበት ዋና ዋና ምክንያቶች፦

1. ​Anchor Bolt Pocket Creation: ለብረት ስትራክቸር (Steel Columns) የሚያገለግሉ Anchor Bolts ኮንክሪቱ ከደረቀ በኋላ በትክክለኛው Alignement ለመትከል እና Grouting ለማድረግ ቦታ ለማዘጋጀት።

2. ​Post-tensioning / Ground Anchors: ፋውንዴሽኑ ከስር ካለው አፈር ወይም ድንጋይ ጋር በጥብቅ እንዲያያዝ ለጂኦቴክኒካል አሬንጅመንት (Ground Anchors/Micro-piles) ማስገቢያ ቀዳዳ ለማዘጋጀት።

3. ​Plumbing/Utility Penetrations: አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የውሃ እና የፍሳሽ መስመሮች በኮንክሪት አካል ውስጥ ማለፍ እንዲችሉ አስቀድሞ ቦታ ለማዘጋጀት (Sleeving)።

https://t.me/ethioengineers1
❤11👍3
August 21, 2026 4K 15